መሥዋዕት
Meswaet
4:34 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ከተከሸኑ እልፍ ቃላት
ከተመረጠ የቅኔ ብዛት
ሀገሩን ከሞላው ዜማ
የኔ ሕይወት ላንተ ይሰዋ/ይሰማ
ቢዘምርልህ ይህ አንደበቴ
መልክህ በራቀው የእለት እለት ህይወቴ
መስዋዕቴ ላንተ እኮ ነው
የሌለህበት ላንተ ምንህ ነው
መስዋዕቴ ላንተ እኮ ነው
ያልከበርክበት ሁሉ ድካም ነው
አዝማች · Chorus
ይዘምር የእልፍኝ ሕይወቴ
አምልኮዬ ይቅደም በቤቴ
ልሁነው የዘመርኩትን
በቃላት ያሰፈርኩትን
ያምልክህ የጓዳ ህይወቴ
ይዘምር ይቅደም በቤቴ
ልሁነው የዘመርኩትን
በዜማ ያመለኩትን
ላምልክህ በህይወቴ በህይወቴ
ይገዛ መላው እኔነቴ ላምልክህ በህይወቴ
ላምልክህ በህይወቴ በህይወቴ
ይገዛ መላ'ው ሰውነቴ ላምልክህ በህይወቴ
ቁጥር 2 · Verse 2
ላንተ መስዋዕት ይህ አይደል ወይ
ያንተ ምስጋና ህይወት አይደል ወይ
ያምልክህ መላው እኔነቴ - ላምልክህ በሕይወቴ
ላንተ መስዋዕት ንፁህ አይደል ወይ
ያንተ ምስጋና ህይወት አይደል ወይ
ያምልክህ መላው ሰውነቴ ላምልክህ በሕይወቴ
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ