Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

አየሱስ ፍቅር

Eyesus Fiker

ትራክ 11 · 6:23 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

የማያረጅ መውደድ የማይቀያየር

ወረት የማያውቀው እውነተኛ ፍቅር

የኢየሱስ ፍቅር ነው

የማያረጅ መውደድ የማይቀያየር

ወረት የማያውቀው የሕይወት ሁሉ ሥር

የኢየሱስ ፍቅር

የጌታዬ ፍቅር

የፍቅርን ትርጉም አትፈልጉት የትም

ከኢየሱስ በስተቀር የትም አይገኝም

ነፍሱን በመስቀል ላይ ሰጠን በጭንቅ አልፎ

እንደሰው ተገኘ ክብሩን አሳልፎ

የኢየሱስ ፍቅር

የጌታዬ ፍቅር

ሐብታም ደሀ የለም ሁሉም ይወደዳል

የሚናቅ ነፍስ የለም ሁሉን ይፈልጋል

ፍቅሩ እንደባህር ነው የማይነጥፍ ዘላለም

ለሰው ልጅ በሙሉ ቢቀዳ አይጎድልም

የኢየሱስ ፍቅር

የጌታዬ ፍቅር

ማይለወጥ የማይናወጥ ፍቅር ኢየሱስ ነው

ማይመዘን የማይለካ ዘላለም ውድ ነው

ማይናወጥ የማይለወጥ ፍቅር ኢየሱስ ነው

ማይመዘን የማይለካ ዘላለም ሚወደው

ኢየሱስ ፍቅር ነው

ጌታዬ ፍቅር ነው

የሕይወት ምንጭ

ኢየሱስ ፍቅር

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ