ደስ ይበለን
Des Yebelen
2008 · ትራክ 1 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
እያንዳንዱ ቀን ክፉ ነው
መልካም መዓዛ ጣዕምም የለው
የትም ብንሄድ ምንም ብንይዝ
ሁሉም ነገር አለው መዘዝ
ነገር ግን ዓይኖቻችንን ወደ ጌታ ስናቀና
የሚያስደስተን ብዙ ነው የሚሞላን በምሥጋና
እስቲ የላዩን እናስብ የምድሩን እንተወውና
አዝማች · Chorus
ደስ ይበለን (፬x)
ሃሴት እናርግ ዕልል እንበል
ቁጥር 2 · Verse 2
በምድር ጥበብ ጥበበኞች
ሃያላን ባላባቶች
ብርቱዎችም ደግሞ እያሉ
የሰውን ምስፈርት የሚያሟሉ
ሥጋን የለበሰ ሁሉ እንዳይመካ በከንቱ
የዓለምን ሞኝ ምናምንቴ ደካማዎችን መምረጡ
የሚያስፈነድቅ ተዓምር ነው እንደ እኛ ዓይነቱን መጥራቱ
አዝማች · Chorus
ደስ ይበለን (፬x)
ሃሴት እናርግ ዕልል እንበል
ቁጥር 3 · Verse 3
በልዩ ልዩ ፈተና ሃዘን ዛሬ ቢጐበኘንም
እምነታችን እንዲነጥር ፈትና ቢደርስብንም
ከተዘጋጀልንና ሊገለጥልን ካለው ክብር
ልንወርሰው ከምንጥብቀው ከማይጠፋው ርስታችን ጋር
ሲመዛዘን ሥፍራም የለው ከቶም አይገባም ከቁጥር
ቁጥር 4 · Verse 4
እግዚአብሔር አምላክ ነው ደስ ይበለን
እኛም ደግሞ ሕዝቡ ደስ ይበለን
በክርስቶስ ዋጅቶን ደስ ይበለን
አርጐናል ገንዘቡ ደስ ይበለን
ከሞት መንጋጋ ውስጥ ደስ ይበለን
ነጥቆ አውጥቶናል ደስ ይበለን
በክንዱ መድሃኒት ደስ ይበለን
ሕያዋን አርጐናል ደስ ይበለን
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ