ምህረቱ
Meheretu
2008 · ትራክ 5 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ምህረቱ እንደ ደመና (፪x) ከቦኛል
ልዘምር የአምላኬን ምሥጋና (፪x)
የዘወትር ትዝታው ማስታወሻው
እኔን ባየኝ ቁጥር ትዝ የሚለው
የሕይወት እስትንፋስ የሆነልኝ
ከምህረቱ በቀር ምንም የለኝ
ጽድቄ ቅድስናዬ ቤዛነቴም ኢየሱስ ነው
የመዳን ልብሴ መጐናጸፊያዬም እርሱ ነው
ቁጥር 2 · Verse 2
ትልቅ ልግስናው ቸርነቱ
ብቃት ሆኖ ያቆመኝ በፊቱ
የማንነቴ ምንጭ መገኛዬ
ይቅርታው እኮ ነው የጌታዬ
ነፍሱን ሰጥቶ ነፍሴን የተቤዛት ኢየሱስ ነው
በደሙ አጥቦ አዲስ ንፁህ ያደረጋት እርሱ ነው
ቁጥር 3 · Verse 3
የረከሰ ማንነቴን ሽሮ
አደፋውን ታሪኬን ቀይሮ
በወይኑ ግንድ ላይ የተከለኝ
በአደባባዮቹም ያበቀለኝ
አክሊል እንደለበሰ ሙሽራ ያስዋበኝ ኢየሱስ ነው
ሞገስ ደም ግባት ዝርግፍ ጌጥ የሆነኝ እርሱ ነው
አዝማች · Chorus
በምህረቱ ልጁ ሆኛለሁ
በምህረቱ ቤቱ ኖራለሁ
በምህረቱ አመልከዋለሁ
በምህረቱ አገለግላለሁ
ምህረቱ ሕይወቴ ምህረቱ ጉልበቴ
ምህረቱ ብቃቴ ምህረቱ ትምክህቴ
ምህረቱ እረፍቴ ምህረቱ ምችቴ
ምህረቱ ተድላዬ ምህረቱ ጥላዬ
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ