የከበበኝ
Yekebebegn
2008 · ትራክ 4 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
የከበበኝ የደገፈኝ አሃሃ
የቀደመኝ የተከተለኝ (፪x)
አምላኬ ነው የሚያኖረኝ (፮x)
እግዚአብሔር ነው
ቁጥር 1 · Verse 1
የጓደኛዬ ነገር የአየሩ ሁኔታ
የዘመን ወጣ ውረድ የጠላት ድንፋታ
አይደለም ሚዛኔ ነገን የምለካበት
ቃልኪዳን ይዣለው እምነቴን የምጥልበት
እርሱ አይለወጥም አምላኬ አይለወጥም
እግዚአብሔር አይለወጥም
ስለዚህ እኔ አልጠፋም (፫x)
አዝማች · Chorus
የከበበኝ የደገፈኝ አሃሃ
የቀደመኝ የተከተለኝ (፪x)
አምላኬ ነው የሚያኖረኝ (፮x)
እግዚአብሔር ነው
ቁጥር 2 · Verse 2
የጨባጭ መረጃ ቢያቀብለኝ ኖሮዬ
እኔም መረጃ አለኝ ቃል ሰጥቶኛል ጌታዬ
እስከ ዛሬ ድረስ አቤነዘር ብያለሁ
ትናንት የረዳኝን ነገም እታመነዋለሁ
እርሱ አይለወጥም አምላኬ አይለወጥም
እግዚአብሔር አይለወጥም
ስለዚህ እኔ አልጠፋም (፫x)
ቁጥር 3 · Verse 3
የክብር አምላክ የክብር
አብሮኝ ሆነና እግዚአብሔር
ያስጨነቀኝ አዋረዳቸው
እንደ መንገድ ጭቃ ረገጣቸው
የክበር ንጉሥ የክብር
ቀድሞኝ ወጣና እግዚአብሔር
ጠላቶቼን ሁሉ አወካቸው
እንደ ትብያ እንደ እብቅ በተናቸው
እርሱ አይለወጥም አምላኬ አይለወጥም
እግዚአብሔር አይለወጥም
ስለዚህ እኔ አልጠፋም (፫x)
ቁጥር 4 · Verse 4
መብልና መጠጥ የድንኳኔ ውበት
መቀበሪያ ሥፍራ የአሟሟቴም ዓይነት
አይደለም ጭንቀቴ እኔን የሚያሳስበኝ
ከዚህ የሚሻገር የደመቀ ተስፋ አለኝ
እርሱ አይለወጥም አምላኬ አይለወጥም
እግዚአብሔር አይለወጥም
ስለዚህ እኔ አልጠፋም (፫x)
አዝማች · Chorus
የከበበኝ የደገፈኝ አሃሃ
የቀደመኝ የተከተለኝ (፪x)
አምላኬ ነው የሚያኖረኝ (፮x)
እግዚአብሔር ነው
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ