Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

መተኪያ የሌለህ

Metekiya Yelieleh

2008 · ትራክ 10 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ያለ አማጭ ታስፈልገኛለህ (፬x)

መተኪያ የሌለህ (፫x) ኢየሱስ ጌታዬ ነህ

በድስታዬ በሃዘኔም ብበለፅግ ብደኸይም

ታስፈልገኛለህ (፪x)

በጥጋቤ በረሃቤም በጤናዬም በህመሜም

ታስፈልገኛለህ (፪x)

ማንም (፫x) አይተካህም

ምንም (፫x) አይተካህም

በጉብዝናዬ በድካሜም ሲሳካልኝ ሳስይካም

ታስፈልገኛለህ (፪x)

በእርካታዬም በጥማቴም በአደባባይ በጓዳዬም

ታስፈልገኛለህ (፪x)

ማንም (፫x) አይተካህም

ምንም (፫x) አይተካህም

ለጠቢቡ ለአዋቂዉም ለታናሹ ለታላቁም

ታስፈልገኛለህ (፪x)

ለታጀበው ለብቸኛውም ለእርሱሙ ሰው ለንጉሡም

ታስፈልገኛለህ (፪x)

ማንም (፫x) አይተካህም

ምንም (፫x) አይተካህም

የሕይወት ምንጭ ነህ (፪x)

የሕይወት እንጀራ የሕይወት ውኃ ነህ

የሕይወት ምንጭ ነህ

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ