ነገሩ ተገለበጠ
Negeru Tegelebete
2008 · ትራክ 2 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ተሳዳጅ እፎይ ሲል አሳዳጅ ሬሳበሬሳ
እግዚአብሔር ክንዱን ሲያነሳ
ጭንቅ ውስጥ አገባቸው አሳያቸው ፍዳ አበሳ
አንሸሽም ቢሉ የማይሆን ሆነ ነገሩ
ሠራዊቱ ታወከ መንከራኩሮቹ ታሰሩ
ባሕሩ ከደናቸው ደግሞ ሳይተያዩ
እስራኤል ተሻገረ ለዘለዓለም ተለያዩ[1]
አዝማች · Chorus
ነገሩ ተገለበጠ
እግዚአብሔር ሕዝቡን አስመለጠ
ነገሩ ተገለበጠ
አዋጅ በአዋጅ ተሻረ
ሞት በሕይወት ተቀየረ
ቁጥር 2 · Verse 2
እግዚአብሔር ተነሳ ንጉሡን እንቅልፍ ነሳው
የተዘጋን መዝገብ እንዲያገላብጥ አደረገው
መታሰብ ሆነና ሃዘን በደስታ ተተካ
ሁኔታው ሲለወጥ ሰቃይ ተሰቃይ ነው ለካ
ዋይታና ስቃይ ጭንቀት ሃፍረት ለጠላታቸው
በአይሁድ የተድላና የደስታ ቀን ሆነላቸው[2]
አዝማች · Chorus
ነገሩ ተገለበጠ
እግዚአብሔር ሕዝቡን አስመለጠ
ነገሩ ተገለበጠ
አዋጅ በአዋጅ ተሻረ
ሞት በሕይወት ተቀየረ
ቁጥር 3 · Verse 3
ከአምላካቸው በቀር ቅዱሳን ስግደት አያውቁም
ሚቆጣ ቢቀጣ ጣዖትን ከቶ አያመልኩም
ሰባት እጥፍ ቢነድ እቶኑ ቢብስበትም
ያድናል እርሱ አንሰግድም ባያድነንም
የጣሏቸው ሰዎች ወሳፈን ገደላቸው
የልዑል አምላክ ባሮች ክብር ተጨመረላቸው[3]
አዝማች · Chorus
ነገሩ ተገለበጠ
እግዚአብሔር ሕዝቡን አስመለጠ
ነገሩ ተገለበጠ
አዋጅ በአዋጅ ተሻረ
ሞት በሕይወት ተቀየረ
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ