የእግዚአብሔር ቃል
YeEgziabhier Qal
2008 · ትራክ 9 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ሃብቴ ነው ሃብቴ ሃኪሜም መድኃኒቴ
ከሞት ጉዞ መለሰኝ በሕይወት ጐዳና መራኝ
ዝናብ ምድርን እንዲያርስ ውስጤን አረስርሶታል
ለአምላኬ ክብር እንድኖር ለፅድቅ አነቃቅቶኛል
አዝማች · Chorus
የእግዚአብሔር ቃል ይባረክ (፬x)
ቁጥር 2 · Verse 2
. (1) . አስደነቀኝ ፈተሸኝ መረመረኝ
ከክፉ . (2) . መክሮ በልቤ ተሰውሮ
ማስተዋሌን አስፈትቶ በትዕዛዙ ሮጣለሁ
የእለት መመሪያዬ አስተዳዳሪዬም ነው
አዝማች · Chorus
የእግዚአብሔር ቃል ይባረክ (፬x)
ቁጥር 3 · Verse 3
ከመጻሐፍት በኩር ታላቅ መጽሐፍት
የማይለወጥ የማይሻር
መጽሐፍ ቅዱስ የአምላኬ ቃል (፪x)
ከሐዘን መጽናኛዬ ቀን ሙሉ ትዝታዬ
ሆኖኝ ወድጄዋለሁ ዘወትር አጫዋቼ ነው
ስስት ይገስፀኛል ስዝል ያበረታኛል
ከስንቁ በልጦብኛል ነፍሴን ሕያው አድርጓታል
ለእግሬ ምብራት ነው
ለመንገዴም ብርሃን ነው
ከየት እንደተገኘሁ ለምን በምድር እንዳለሁ
በኋላም መድረሻዬን አሳየኝ ገልጦ ዓይኔን
ቁም ነገረኛ አድርጐ ውብ ዓላማ አስጨበጠኝ
እንደ ሌላ ለውጦ ከሰውም ሰው አረገኝ
አዝማች · Chorus
የእግዚአብሔር ቃል ይባረክ (፬x)
ቁጥር 4 · Verse 4
ከመጻሐፍት በኩር ታላቅ መጽሐፍት
የማይለወጥ የማይሻር
መጽሐፍ ቅዱስ የአምላኬ ቃል (፪x)
እንዱ ከድኖ ሲስመው ሌላው ሲንተራስበት
አንዱ ተረት ሲመስለው ሌላው ሲያላግጥ
ለእኔ ግን ሆኖኛል የማይዘለቅ በረከት (፪x)
ቁጥር 5 · Verse 5
ብሰማው ብሰማው ማዳምጠው ማዳምጠው
ሁሌ አዲስ ነው ሁሌ አዲስ ነው
ባነበው ባነበው ባጠናው ባጠናው
የእግዚአብሔር ቃል ይባረክ (፬x)
ቁጥር 6 · Verse 6
ከመጻሐፍት በኩር ታላቅ መጽሐፍት
የማይለወጥ የማይሻር
መጽሐፍ ቅዱስ የአምላኬ ቃል (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ