ዛሬም ይኸውልህ
Zariem Yeheweleh
2008 · ትራክ 3 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
በዘመናት . (1) . ግን አላረጀህም
የዓመታት እርዝማኔ አላታከተህም
ትናንት ዛሬ ለዘለዓለም አንተ ያው አንተ ነህ
አዝማች · Chorus
ኃያል ንጉሥ እግዚአብሔር የምትገርም አምላክ ነህ (፭x)
ቁጥር 2 · Verse 2
እንኳን አመለኩህ አንኳን ሰገድኩልህ
ገናም አልበቃኝም ዛሬም ይኸውልህ
አዲስ ምሥጋና (፬x) ዛሬም ይኸውልህ (፭x)
ቁጥር 3 · Verse 3
ማልጄ ልዘምር ደግሞም ቀን በቀትር
ምሽትም ጨምራለሁ ይኼም ሲያንስህ ነው (፪x)
ምሥጋናዬ አይነስህ ይደራረብ በመቅደስህ (፪x)
ቁጥር 4 · Verse 4
ብዙ አማልክት ወድቀዋል ለጥቂት ተደንቀው(?)
መታሰቢያ እንኳን አጥተዋል ዘመን አልፎባቸው
አንተ ግን እንዳማረብህ በዙፋንህ ላይ ነህ
አዝማች · Chorus
ኃያል ንጉሥ እግዚአብሔር እጅግ ድንቅ አምላክ ነህ (፭x)
ቁጥር 5 · Verse 5
እንኳን አደነኩህ እንኳን ሰገድኩልህ
ገናም አልበቃኝም ዛሬም ይኸውልህ
አዲስ ምሥጋና (፭x) ዛሬም ይኸውልህ (፭x)
ቁጥር 6 · Verse 6
በታላላቅ ጉባኤ በጓዳም ለብቻዬ
መስዋዕቴ ያርግልህ ጣፋጭ መዓዛ ይሁንልህ (፪x)
አምልኮዬ አደነልህ ይደራረብ በመቅደስህ (፪x)
ቁጥር 7 · Verse 7
ፍቅር ምህረት ቸርነትህ ማልዶ ማልዶ አዲስ ነው
አሮጌ ታሪክ የለህም ብርታትህም ያው ነው
የቅድስናህም ክብር እያደር ይደምቃል
አዝማች · Chorus
ኃያል ንጉሥ እግዚአብሔር ዝናህ ምድርን ሞልቷል (፭x)
ቁጥር 8 · Verse 8
እንኳን አወደስኩህ እንኳን ዘመርኩልህ
ገናም አልበቃኝም ዛሬም ይኸውልህ
አዲስ ምሥጋና (፭x) ዛሬም ይኸውልህ (፬x)
ቁጥር 9 · Verse 9
ካየሁት ከሰማሁት ለነፍሴ የቀረላት
በአንተ መደነቅ ነው ዋናም ትርፍም የሆነላት (፪x)
አዝማች · Chorus
ምሥጋናዬ አይነስህ
ዝማሬ አይነስህ
አምልኮዬ አይነስህ
አክብሮት አይነስህ
ይደራረብ በመቅደስህ
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ