እግዚአብሔር አለ
Egziabhier Ale
ትራክ 2 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
የአብርሃም የይስሃቅ የያዕቆብ አምላክ
ዛሬም በቅዱስ ማደሪያው አለና
ሥጋ ለባሽ ሁሉ በፊቱ ዝም ይበል
እግዚአብሔር አለና
አዝማች · Chorus
የምድር ዳርቻ ፈጣሪ
ለዘለዓለምም ነዋሪ
ማይደክም ማይታክተዉ
ማስተዋሉ ማይመረመረዉ
እግዚአብሔር አለ በማደሪያው
እግዚአብሔር አለ በከፍታው
ቁጥር 2 · Verse 2
ለደካማ ኃይልን ይሰጣል
ጉልበት ላጣው ብርታት ይጨምራል
በጽድቁ ቀን ደግፎ ይይዛል
እግዚአብሔር ህዝቡን መቼ ይተዋል (፪x)
አዝማች · Chorus
የምድር ዳርቻ ፈጣሪ
ለዘለዓለምም ነዋሪ
ማይደክም ማይታክተዉ
ማስተዋሉ ማይመረመረዉ
እግዚአብሔር አለ በማደሪያው
እግዚአብሔር አለ በከፍታው
ቁጥር 3 · Verse 3
ወፎችን በእፍኙ የሰፈረ
ሠማይን በስንዝር የለካዉ
ከፍ ባለ ዙፋን ላይ የተቀመጠው
ለትውልድ ሁሉ መጠጊያ ነው
አዝማች · Chorus
የምድር ዳርቻ ፈጣሪ
ለዘለዓለምም ነዋሪ
ማይደክም ማይታክተዉ
ማስተዋሉ ማይመረመረዉ
እግዚአብሔር አለ በማደሪያው
እግዚአብሔር አለ በከፍታው
ቁጥር 4 · Verse 4
ስለድሆች መከራ ስለችግረኞች
ጌታዬ ይመጣል ወደመቅደሱ በድንገት
የወደቀ ይነሳል የሳተ ይመለሳል
በእግዚአብሔር ጉብኝት ገና ጠላት ይቃጠላል
ተስፋ የቆረጣችሁ በእምነት ደክማችሁ
በጠላትም ዛቻ አንገት የደፋቹህ
አምላካቹህ በበቀል በእርግጥ ይመጣል
የእናንተም ደስታ ገናስ ከሩቁ ይሰማል
ያዕቆብ ሆይ እስራኤልም ሆይ
አልሰማህም ወይ አላወቅክም ወይ (፪x)
መንግዴ ከእግዚአብሔር ተሰውራለች
ፍርዴም ከአምላኬ ደግሞም አልፋለች
ለምን ትላለህ ለምንስ እንዲህ ትናገራለህ
አልሰማህም ወይ አላወክህም ወይ
የእኛ ጌታ አለ (አለ) እንደነገሠ (አለ)
አላረጀም (አለ) አልደከመም (አለ)
አይታክትም (አለ) አለ ጌታ (አለ)
አለ ጌታ (አለ) ትናንትናም ዛሬም (አለ)
ነገም ለዘለዓለም (አለ) ያው ነው ኢየሱስ (አለ)
አለ ጌታ (አለ) አለ ጌታ (አለ)
አለ ውዴ (አለ) አለ ጌታ (አለ አለ)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ