Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ኑሮን ለዘለዓለም

Nuron Lezelealem

ትራክ 8 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

አቤቱ ፈውሰን እኛም እንፈወሳለን

አቤቱ መልሰን እኛም እንመለሳለን (፪x)

ቃልኪዳንና ሚሉትን የምትጠብቅ

ታላቅና ሃያል የተፈራህ አምላክ

በደረሰብን ነገር ሁሉ አንተ ጻዲቅ ነህ

ቤትህን መልስልን ጉስቁልናችንን አይተህ

አቤቱ ፈውሰን እኛም እንፈወሳለን

አቤቱ መልሰን እኛም እንመለሳለን (፪x)

እንደበደላችን አታድርግብን

እንደኀጢአታችንም አትክፈለን

እጠበን ጌታ ሆይ እኛም እንነጻለን

ከበረዶ ይልቅ ነጭ እንሆናለን

አቤቱ ፈውሰን እኛም እንፈወሳለን

አቤቱ መልሰን እኛም እንመለሳለን (፪x)

በብዙ እንግዳ ነገር ረክሰናል

የተወደደው እርሻ በባሕር ተረግጧል

ጠላትም በቤትህ ጓዳ ይኖራል

የተቀደሰው እቃ ለብዝበዛ ሆኗል

አቤቱ ፈውሰን እኛም እንፈወሳለን

አቤቱ መልሰን እኛም እንመለሳለን (፪x)

ከአመጻችን ብዛት መንፈስህን አስመረርን

እጅግ አስቆጣንህ በእምቢተኝነታችን

አንተ ግን ምህረትህ የበዛ አምላክ ነህ

ታደገን አባት ሆይ ስለስምህ ብለህ

አቤቱ ፈውሰን እኛም እንፈወሳለን

አቤቱ መልሰን እኛም እንመለሳለን (፪x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ