ታላቅና የተፈራህ
Talaqena Yeteferah
ትራክ 4 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
እልፍ አእላፋት መላዕክት ከፊትህ እየሰገዱ
ቅዱስ ቅዱስ እያሉ ሁሌ የሚያመልኩህ
በረከትና ክብር ምሥጋናም ሃይልም
ለአንተ ለቅዱሱ ይሁን ለዘለዓለም
አዝማች · Chorus
ታላቅና የተፈራህ አምላክ
በቅድስናህ የከበርህ ጌታ
ከፍ ካለ ዙፋን ላይ በከፍታ ያለህ
ቅዱስ (፫x) እግዚአብሔር
በሰማይና በምድር ታላቁ ስምህ ይክበር
ቁጥር 2 · Verse 2
ከዘመናት ሁሉ ክብርህን ጠብቀህ
ሳትሻር ሳትለወጥ በዙፋንህ ጸንተህ
ያለህና የነበርህ ሁሉን ምትገዛ አምላክ
በምሥጋና ከፍ ያለው ክቡር ስምህ ይባረክ
አዝማች · Chorus
ታላቅና የተፈራህ አምላክ
በቅድስናህ የከበርህ ጌታ
ከፍ ካለ ዙፋን ላይ በከፍታ ያለህ
ቅዱስ (፫x) እግዚአብሔር
በሰማይና በምድር ታላቁ ስምህ ይክበር
ቁጥር 3 · Verse 3
ማለዳ እጅግ ተሞልቶ ከክብርህ ታላቅነት
አምልኮ ለአንተ ይቀርባል ዘወትር ቀንና ሌሊት
ሃያልና ባለብዙ ግርማ ሞገስ
እንደአንተ የለምና ለዘለዓለም ንገሥ
አዝማች · Chorus
ታላቅና የተፈራህ አምላክ
በቅድስናህ የከበርህ ጌታ
ከፍ ካለ ዙፋን ላይ በከፍታ ያለህ
ቅዱስ (፫x) እግዚአብሔር
በሰማይና በምድር ታላቁ ስምህ ይክበር
ቁጥር 4 · Verse 4
ልጽሆም ልጽህር የፈቀድከውን ልታደርግ
ሃይልና ስልጣን ያለህ የወሰንከውን ልትፈጽም
አማካሪና ረዳት ከቶ የማያስፈልግህ
ምንም የማይጐድልህ ፍፁም አምላክ አንተ ነህ
አዝማች · Chorus
ታላቅና የተፈራህ አምላክ
በቅድስናህ የከበርህ ጌታ
ከፍ ካለ ዙፋን ላይ በከፍታ ያለህ
ቅዱስ (፫x) እግዚአብሔር
በሰማይና በምድር ታላቁ ስምህ ይክበር
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ