Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

እግዚአብሔር ከእኔ ጋር ባይሆን ኖሮ

Egziabhier Kenie Gar Bayhon Noro

አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

እግዚአብሔር ከእኔ ጋር ባይሆን ኖሮ በእነዚህ ዓመታት

በክንዱ ደግፎ ባያሻግረኝ ክፉዎቹን ቀናት

አጠገቤ ቆሞ ባያበረታኝ በነውጡ ሰዓት

ሕያው ሳለሁኝ በዋጠኝ ነበር ጠላቴ እንደቁጣው ጽናት (፪x)

የአመጽን ፈሳሽ እያደረቀ የጥፋትን ጎርፍ እየገደበ

ነፍሴን እንደወፍ ከአዳኞች ወጥመድ እያስመለጣት

ላኖረኝ ጌታ እስቲ ልሰዋ የምሥጋናን መስዋዕት

(ሃሌሉያ) ሃሌሉ (ሃሌሉያ) ሃሌሉ...ሃሌሉያ

(ኦ ሃሌሉያ) ሃሌሉ...ሃሌሉ...ሃሌሉያ

በመከራዬ ቀን ልመናዬን ሰማኝ

ከላይ ከመቅደሱ ረድኤቱን ላከልኝ

የጠላቶቼን ከፍታ አስረገጠኝ

በማዳኑ እጅግ ደስ አሰኘኝ (፪x)

(ሃሌሉያ) ሃሌሉ (ሃሌሉያ) ሃሌሉ...ሃሌሉያ

(ኦ ሃሌሉያ) ሃሌሉ...ሃሌሉ...ሃሌሉያ

ለጥርሱ ንክሻ አላደረገኝ

ከተደበቀብኝ ወጥመድ አዳነኝ

ነፍሴን ከመከራ ሁሉ ላዳናት

ለጌታ ለኢየሱስ ዘሬም ይገዛለት (፪x)

(ሃሌሉያ) ሃሌሉ (ሃሌሉያ) ሃሌሉ...ሃሌሉያ

(ኦ ሃሌሉያ) ሃሌሉ...ሃሌሉ...ሃሌሉያ

ምንም ያህል ብዙ ወዳጆች ቢኖሩም

በመከራ ቀን ግን ማንም አይገኝም

ፍፁም ሳይለወጥ ልመናን ሚፈጽም

ታማኙ እግዚአብሔር ይክበር ለዘለዓለም

ፊቱ ሳይቀየር ልመናን ሚፈጽም

ታማኙ እግዚአብሔር ይክበር ለዘለዓለም

(ሃሌሉያ) ሃሌሉ (ሃሌሉያ) ሃሌሉ...ሃሌሉያ

(ኦ ሃሌሉያ) ሃሌሉ...ሃሌሉ...ሃሌሉያ

የተግሳጽና የዘለፋው ብዛት

አቤት በመከራ ቀን የተግዳሮት አይነት

የጠላትን ትዕቢት የጨለማውን ብርታት

በአንዲት/በአፉ ቃል ሽሮ ያከብራል በቅጽበት (፪x)

እግዚአብሔር ከእኔ ጋር ባይሆን ኖሮ በእነዚህ ዓመታት

በክንዱ ደግፎ ባያሻግረኝ ክፉዎቹን ቀናት

አጠገቤ ቆሞ ባያበረታኝ በነዉጡ ሰዓት

ሕያው ሳለሁኝ በዋጠኝ ነበር ጠላቴ እንደቁጣው ጽናት (፪x)

የአመጽን ፈሳሽ እያደረቀ የጥፋትን ጎርፍ እየገደበ

ነፍሴን እንደወፍ ከአዳኞች ወጥመድ እያስመለጣት

ላኖረኝ ጌታ እስቲ ልሰዋ የምሥጋናን መስዋዕት

(ሃሌሉያ) ሃሌሉ (ሃሌሉያ) ሃሌሉ...ሃሌሉያ

(ኦ ሃሌሉያ) ሃሌሉ...ሃሌሉ...ሃሌሉያ

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ