Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ሃሌሉያ

Hallelujah

ትራክ 11 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ሃሌሉያ (፬x)

ከኀጢአት ባርነት ከዘለዓለም ሞት

አዳነን ኢየሱስ እኛን ሰጠን ሕይወት

ፍፁም አምላክ ሲሆን እራሱን አዋረደ

የባሪያውን መልክ ይዞ ከሰማይ ወረደ

በጠና. (1) . ከስፍራው በበረት ተወለደ

ስለኀጢአተኞች ስለእኛ ማለደ

ሃሌሉያ (፬x)

ከኀጢአት ባርነት ከዘለዓለም ሞት

አዳነን ኢየሱስ እኛን ሰጠን ሕይወት

በመስቀል ላይ ለመሞት ፈቃደኛውን

ከዘለዓለም ሞት ሊያድንን ከኩነኔ

የጥልቅ ግድግዳውን በሥጋው አፈረሰ

ለኀጢአት ይቅርታ ደሙን አፈሰሰ

ሃሌሉያ (፬x)

ከኀጢአት ባርነት ከዘለዓለም ሞት

አዳነን ኢየሱስ እኛን ሰጠን ሕይወት

ሰላሳ ሶስት አመት በምድር ላይ ኖረ

የሕይወትን መንገድ ለሰዎች አስተማረ

የሁሎችን በደል እርሱ ተሸከመ

አገልግሎቱን በመስቀል ላይ ፈጸመ

ሃሌሉያ (፬x)

ከኀጢአት ባርነት ከዘለዓለም ሞት

አዳነን ኢየሱስ እኛን ሰጠን ሕይወት

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ