ነፍሴ ሆይ
Nefsie Hoy
ትራክ 7 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
"የአብርሃም የይሳቅ የያዕቆብ አምላክ
ዛሬም በቅዱስ ማደሪያው አለና
ሥጋ ለባሽ ሁሉ በፊቱ ዝም ይበል
እግዚአብሔር አለና እግዚአብሔር አለና"
አዝማች · Chorus
የምድር ዳርቻ ፈጣሪ ለዘለዓለምም ነዋሪ
ማይደክም ማይታክተው ማስተዋሉ ማይመረመረዉ
እግዚአብሔር አለ በማደሪያው
እግዚአብሔር አለ በከፍታው
ቁጥር 2 · Verse 2
ልደካማ ሃይልን ይሰጣል
ጉልበት ላጣው ብርታት ይጨምራል
በጽድቁ ቀን ደግፎ ይይዛል
እግዚአብሔር ህዝቡን መቼ ይተዋል (፪x)
አዝማች · Chorus
የምድር ዳርቻ ፈጣሪ ለዘለዓለምም ነዋሪ
ማይደክም ማይታክተው ማስተዋሉ ማይመረመረዉ
እግዚአብሔር አለ በማደሪያው
እግዚአብሔር አለ በከፍታው
ቁጥር 3 · Verse 3
ወፎችን በእፍኙ የሰፈረው
ሰማይን በስንዝር የለካው
ከፍ ባለ ዙፋን ላይ የተቀመጠው
ለትውልድ ሁሉ መጠጊያ ነው
አዝማች · Chorus
የምድር ዳርቻ ፈጣሪ ለዘለዓለምም ነዋሪ
ማይደክም ማይታክተው ማስተዋሉ ማይመረመረዉ
እግዚአብሔር አለ በማደሪያው
እግዚአብሔር አለ በከፍታው
ቁጥር 4 · Verse 4
ስለደሆች መከራ ስለችግረኞች
ጌታዬ ይመጣል ወደመቅደሱ በድንገት
የወደቀ ይነሳል የሳት ይመለሳል
በግዚአብሄር ጉብኝት ገና ጠላት ይቃጠላል
ተስፋ የቆረጣችሁ በእምነት የደክማችሁ
በጠላትም ዛቻ አንገት የደፋቹህ
አምላካቹህ በበቀል በእርግጥ ይመጣል
የእናንተም ደስታ ገና ከሩቅ ይሰማል
ያዕቆብ ሆይ እስራኤልም ሆይ
አልሰማህም ወይ አላወቅህም ወይ (፪x)
መንገዴ ከእግዚአብሔር ተሰውራለች
ፍርዴም ከአምላኬ ደግሞም አልፋለች
ለምን ትላለህ ለምንስ እንዲህ ትናገራለህ
አልሰማህም ወይ አላወቅህም ወይ
የኛ ጌታ አለ (አለ) እንደነገሠ (አለ)
አላረጀም (አለ) አልደከመም (አለ)
አይታክትም (አለ) አለ ጌታ (አለ)
አለ ጌታ (አለ) ትላንትናም ዛሬ (አለ)
ነገም ለዘለዓለም (አለ) ያው ነው ኢየሱስ (አለ)
አለ ጌታ (አለ) አለ ጌታ
አለ ውዴ (አለ) አለ ጌታ (አለ)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ