እግዚአብሔር የታል ለምን ትለኛለህ
Egziabhier Yetal Lemen Telegnaleh
2010 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
እግዚአብሔር የታል ለምን ትለኛለህ
ፍጥረታት በዙሪያህ ከበውህ እያየህ
ዓይን አጥርቶ ቢያይ ጆሮችህ ቢያቀኑ
የእርሱን ህልውና ታይ ነበር በውኑ
ውጣ ወደ ሜዳው ሂድ ወደ ሃይቁ
የፍጥረትን ሰሪ ቢያሻህ መጠየቁ
አቀበቱን ውጣ ቁልቁለቱን ውረድ
ሜዳ ለጥ ያለውን ወይ ረዥሙን መንገድ
በደረስክበቱ የሰማህ ያየኸው
ሰሪና ተካዩ ሕያው እግዚአብሔር ነው
እያት ቢራቢሮ ተፈጥሮ ያስጌጣት
ክንፎቹዋ ርግብግብ ውበት የተሰጣት
ተመልከት ወፊቱን ጐጆ ስትራ
መሰረቱን ጥላ ለፍታ ጥራ ግራ
የትም ዞራ ዞራ በአየር በደመና
ተመልሳ ቤቷ ሳትስት ጐዳና
አዝማች · Chorus
እግዚአብሔርን በእጅህ ቢያሻህ ለመዳሰስ
የልብህን ጥያቄ ምናልባት ቢመለስ
ተመልከት ፍጥረትን የሰራውን በእጁ
ወጥተህ ወደ ደጁ
ቁጥር 2 · Verse 2
እግዚአብሔር የታል ለምን ትለኛለህ
ፍጥረታት በዙሪያህ ከበውህ እያየህ
ዓይን አጥርቶ ቢያይ ጆሮችህ ቢያቀኑ
የእርሱን ህልውና ታይ ነበር በውኑ
ነፋሱም ያፏጫል ዛፉም ይራወጣል
ጂረቱም ይፈሳል ምንጩም ያው ይፈልቃል
ቀን ለፀሐይ መውጫ ማታው ለጨረቃ
ጨለማና ብርሃን በተራ ጥበቃ
ወቅት ሲፈራረቅ ዛሬም እንደጥንቱ
እግዚአብሔር ያውልህ እየው በፍጥረቱ
ከፀሐይ ባሻገር ብዙ ዘመን ርቀት
እልፍ አእላፍ ክዋክብት ያሸበረቀበት
ዓሣ ነባሪውም በውቂያኖስ ጥልቀት
አናብስቱ በዱር ሲያገሱ በርቀት
ገብረ ጉንዳን ሰልፉ ሁከት የሌለበት
ውብ ፍጥረት ዙሪያህን አልመጣ እንደድንገት
አዝማች · Chorus
እግዚአብሔርን በእጅህ ቢያሻህ ለመዳሰስ
የልብህን ጥያቄ ምናልባት ቢመለስ
ተመልከት ፍጥረትን የሰራውን በእጁ
ወጥተህ ወደ ደጁ
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ