ይነጫነጭ ጠላት
Yenechanech Telat
2010 · ትራክ 5 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
ፀሐይ ፈነጠቀች ደረሰ ጠዋቱ
ድምጼም ያስተጋባ የገደል ማሚቱ
እግዚአብሔርን ልጥራ በውዳሴ አሃዱ
ይነጫነጭ ጠላት ያው እንደልማዱ (፫x)
ቁጥር 1 · Verse 1
ተመቻችቶ ነበር እርስቱን አስፍቶ
ዝምታዬ ጣፍጦት ሲቧርቅ ሰንብቶ
ስለቴ ደርሶልኝ ለእግዚአብሔር ብዘምር
ሽብር ተፈጠረ በዲያብሎስ ቅጥር
በማለዳ ዜማ እግዚአብሔር ከበረ
ክፋት ሸራቢው ግን ዲያብሎስ አፈረ
እርሱ እንዳሻው ይሁን የሲኦሉ ሲሳይ
እኔ ግን ልዘምር ላለው ዙፋኑ ላይ
በክረምት በበጋ በህመም በጤና
በክብር በውርደት በድል እንደገና
በማግኘት በማጣት በትርፍ በኪሳራ
ስንቱን አቋርጠናል ከእግዚአብሔር ጋራ
አዝማች · Chorus
ፀሐይ ፈነጠቀች ደረሰ ጠዋቱ
ድምጼም ያስተጋባ የገደል ማሚቱ
እግዚአብሔርን ልጥራ በውዳሴ አሃዱ
ይነጫነጭ ጠላት ያው እንደልማዱ (፫x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ዙሬያየን የማየው እልልም ባያሰኝ
የክብሩን መስዋእት ልነፍግ እኔ ማን ነኝ
በዘመነ መልካም ወይ ዘመን ቁዛሜ
እወድሰዋለሁ በሰዎች ፊት ቆሜ
ጆሯችንን ሰርቆ ሹክ የሚለን ጠላት
ሰፍሮ ትከሻችን ሲጭንብን መዓት
ማርከሻው መዝሙር ነው ለእግዚአብሔር ምሥጋና
ጥንትም የኢየሱስ ሥም መች ይበገርና
በክረምት በበጋ በህመም በጤና
በክብር በውርደት በድል እንደገና
በማግኘት በማጣት በትርፍ በኪሳራ
ስንቱን አቋርጠናል ከእግዚአብሔር ጋራ
አዝማች · Chorus
ፀሐይ ፈነጠቀች ደረሰ ጠዋቱ
ድምጼም ያስተጋባ የገደል ማሚቱ
እግዚአብሔርን ልጥራ በውዳሴ አሃዱ
ይነጫነጭ ጠላት ያው እንደልማዱ (፫x)
ቁጥር 3 · Verse 3
በቃላቶች ውበት ጤም ባለው ዜማ
ተነሱ እንወድስ ድምጻችን ይሰማ
የልባችን ክብደት አስጨናቂው ሁሉ
እንደ እያሪኮ ግንብ ይናዳል ከውሉ
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ