Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

የሰው አስታማሚ

Yesew Astamami

2010 · ትራክ 8 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

የሰው አስታማሚ ውሱን ነው ስልቹ

ይርዳሉ እጆቹ ይከብዳሉ ዓይኖቹ

የሰው አስታማሚ ጥቂት ነው ትዕግስቱ

እግዚአብሔር ግን ታማኝ ቅርብ ለጠሩቱ

እግዚአብሔር ግን ታማኝ

በራችሁ ተዘግቶ ተረሳን ያላችሁ

ውኃ ቀና አድርጐ ጠፍቶ የሚያጠጣችሁ

በሩቁም በቅርቡ በያላችሁበት

ቁስላችሁ ይጠገን በጌታ ምህረት

ቁስላችሁ ይጠገን

ማነው የሚገደው ለእነኛ አቅም ላጡት

ፀሐይ ለማይሞቁ ደጅ ለማይውጡ

ከዓይናችን ከጠፉ ፈጥነው ይረሳሉ

ኩርሲያቸው ተወስዶ እያሉ እንደሌሉ

ከአጥር ውዲህ ተከማችተን

ጭፍራ ዝላዩን ትተን

እስቲ እንውጣ ከአዳራሹ

ፍቅር ድጋፍ ወደሚሹ

ፌጦው ድንገተኛው ሁሉ ተሞክሮ

ሃኪሙም ሳይታክት በጥበብ በአይምሮ

በሩቅ በጐረቤት ተመክሮ ተዘክሮ

እልፍ አልተገኘም ተጥሮ ተግሮ

በህክምና ሂደት መድኃኒት ቅመማ

በሳይንስ ጥናት በሊቆች ግምገማ

የዕድሜያችሁ መጽሃፍ ተከድኗል ያሉአችሁ

ወደ ፈዋሽ አምላክ ይመልከት ዓይናችሁ

ወደ ፈዋሽ አምላክ

ማነው የሚገደው ለእነኛ አቅም ላጡት

ፀሐይ ለማይሞቁ ደጅ ለማይውጡ

ከዓይናችን ከጠፉ ፈጥነው ይረሳሉ

ኩርሲያቸው ተወስዶ እያሉ እንደሌሉ

ከአጥር ውዲህ ተከማችተን

ጭፍራ ዝላዩን ትተን

እስቲ እንውጣ ከአዳራሹ

ፍቅር ድጋፍ ወደሚሹ

ህመማችሁ ጸንቶ ቀና የማትሉት

ፋታ የማይሰጣችሁ ውጋት ቀርጥማቱ

ውሉ የጠፋችሁ የቀን የሌሊቱ

ጌታ ይዳብሳችሁ ባላችሁበቱ

በበሽታ አቅምህ የለ

ሥጋ አጥንትህ የሰለለ

በፍራቻ ባሕር ስምጠት

ሰውም ከቦህ ብቸኝነት

ከሃኪሙ ተስፋ አጥተሃል

ጤና አዳሙም ሰልችቶሃል

እዛው ባልጋው ባለህበት

ፈዋሹ አምላክ ይንካህ ድንገት

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ