ታማኝ ሰው ጠፋ
Tamagn Sew Tefa
2010 · ትራክ 10 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ታማኝ ሰው ጠፋ በአገሩ
ታማኝ ሰው ጠፋ በምድሩ
ሰዎች አላገኙም ቢዞሩ ቢዞሩ
በፈረሥም ጠፋ እንኳንስ ሰው በእግሩ
ታማኝ ግን በሰማይ አለ በመንበሩ
በእርጅናዬ ዘመን አንድ እውነት አገኘሁ
አደራ ማይበላ እግዚአብሔር ብቻ ነው
ብዙ ወሰደብኝ ሚስጢሩ ሳይገባኝ
ይሄ ሰው ማመኔ ደህና አድርጐ ጐዳኝ
የዘመናት ጥቅልል የምድር እና ሰማይ
የጌታን መመለስ በሁለት ዐይኖቸ ላይ
ያወኩት ዛሬ ስአቱ መድረሱን
ያበላሁት ወዳጂ ሲያፋጭብኝ ጥርሱን
አዝማች · Chorus
ዘመን ተለዋውጧል (፪x)
በኩርናን በእንጐቻ ሰው ሁሉ ለውጧል
ቁጥር 2 · Verse 2
ጨዋነትና ክበር ውህ ፈሰሰበት
የቃል አምነት ቀርቷል ፊርማ ከሌለበት
ቁጥር 3 · Verse 3
ታማኝ ሰው ጠፋ በአገሩ
ታማኝ ሰው ጠፋ በምድሩ
ሰዎች አላገኙም ቢዞሩ ቢዞሩ
በፈረሥም ጠፋ እንኳንስ ሰው በእግሩ
ታማኝ ግን በሰማይ አለ በመንበሩ
እወየው ጯዋነት ሰፈር ጥሎ ሄዷል
ወገን በወገኑ ያልፍርሃት ነግዷል
ያስቀመጡት እቃ አይገኝም ዳግም
ሁሉ ቃል አጥፊ መሃላ ቢያደርግም
ወንድሞቹ ሸጡት ዮሴፍን ለእንጀራ
ማዕድ የተጋሩት ሆኑት ባላጋራ
የጥንት ታሪክ ነው ዛሬ በዚህ የለም
ብዬ ነበር ኋላ በራሴ ሊፈጸም
አዝማች · Chorus
ዘመን ተለዋውጧል (፪x)
በኩርናን በእንጐቻ ሰው ሁሉ ለውጧል
ቁጥር 4 · Verse 4
ጨዋነትና ክብር ውህ ፈሰሰበት
የቃል እምነት ቀርቷል ፊርማ ከሌለበት
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ