ምህረት አልወረደም
Meheret Alweredem
2010 · ትራክ 9 · አማርኛ
እየመሽ ነጋ እየነጋም መሽ
ዛሬም ጉስቁልና ከምድሪቱ እልሸሸ
ሁካቴ የፀናበት የአልጋ ቁራኛ ሰው
ታሞ ማያገግም ማቁን አለበሰው
ቀባሪ ደከመው ግራ ቅኝ እሬሳ
ሃዘን ተቀማጩም ዛሬም አልተነሳ
ጥቁር የለበሰ የተላጨ ፀጉሩ
ወዳጁን ያጣ ሰው ፈሷል በመንደሩ አሂሂ ፈሷል በመንደሩ
ዛሬም ገና ነው
ገና ነው ምህረቱ አልወረደም
የሃገሬ ንዳድ ዛሬም አልበረደም አዎ
ገና ነው ቁጣው መቸ ሰከነ
በሽታና ርሃብ ባገሬ በወንዜ ገነነ
ከማዶ ይሰማል እሪታ ከሩቅ
የሞት ልጆች ለቅሶ ዋይታ የሚሰቅቅ
አፅናኝ ሆይ ውረድ ወደ ምድር
ምሕረትህ ይጐብኘን ይውደቅ የሞት በትር
አፅናኝ ሆይ
ማረን ጌታችን ፈጽመህ አትቅጣን
ጠበልክን እርጨን ጠምቶናል አጠጣን
ታማሚው ይፈወስ የራበው ሰው ይጥገብ
የፍርድ አዋጅ በቅቶ ምህረቱ ይነበብ
ከትናንት ዛሬ ይሻል ይሆን ብለን
የበጐ ቀን ያለህ አልመጣም ጠብቀን
የነገዋ ፀሐይ ሙቀት ይዛ ትምጣ
የሃገር ልጅ በርዶታል ድሪቶም ስላጣ
በረሃብ ጉስቁልና በጥማት ተቃጥሎ
በብርድ ተጠብሶ በፀሐይ ከሳስሎ
ኑሮ እንደሬት መሮት ለሞቱ የሚጐመጅ
በጐዳናው ከፈፍ ተዘርግቷል እድጅ አሂሂ ተዘርግቷል እደጅ
ዛሬም ገና ነው
ገና ነው ምህረቱ አልወረደም
የሃገሬ ንዳድ ዛሬም አልበረደም አዎ
ገና ነው ቁጣው መቸ ሰከነ
በሽታና ርሃብ ባገሬ በወንዜ ገነነ
ከማዶ ይሰማል እሪታ ከሩቅ
የሞት ልጆች ለቅሶ ዋይታ የሚሰቅቅ
አፅናኝ ሆይ ውረድ ወደ ምድር
ምሕረትህ ይጐብኘን ይውደቅ የሞት በትር
አፅናኝ ሆይ
ማረን ጌታችን ፈጽመህ አትቅጣን
ጠበልክን እርጨን ጠምቶናል አጠጣን
ታማሚው ይፈወስ የራበው ሰው ይጥገብ
የፍርድ አዋጅ በቅቶ ምህረቱ ይነበብ
ክራራይሶ (፪x) እግዚኦ ማሃረነ ክርስቶስ (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ