ተለይተው ከእኛ
Teleyetew Kegna
2010 · ትራክ 4 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
ከሰፈር ሰፈር
ውጭ ጉዋሮው ሳየቀር
ከበራፍ በራፍ
ከቶ አንድም ቤት ሳታልፍ
አጽናኝ መንፈስ ሆይ ፈጥነህ ድረስ ለእኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
የምንወዳቸው ተለይተው ከእኛ
እስከመቼ ድረስ ሆነን ሃዘንተኛ
ሰውማ ዛሬም ላይ ታች ይላል
አደባባዩስ መቼ ይጐላል
ጨዋ ህዝብ ፈገግታ ያሳያል
ልቡ ግን በሃዘን ይጋያል
ወንድ ሴት ልጆቹን ያጣ ሰው
እህቱን ወንድሙን ያጣ ሰው
ወላጆቹን በሞት ያጣ ሰው
ያጽናኝ ያለህ ይላል ሆዱን እየባሰው
አዝማች · Chorus
ከሰፈር ሰፈር
ውጭ ጉዋሮው ሳየቀር
ከበራፍ በራፍ
ከቶ አንድም ቤት ሳታልፍ
አጽናኝ መንፈስ ሆይ ፈጥነህ ድረስ ለእኛ
ቁጥር 2 · Verse 2
የምንወዳቸው ተለይተው ከኛ
እስከመቼ ድረስ ሆነን ሃዘንተኛ
ባልንጀር አብሮ አደጉን ያጣ
የሥራ ባልደራባዉን ያጣ
ጐረቤት ጠያቂውን ያጣ
የሚያጽናናው ዛሬ ከየት ይምጣ
ሞት ያልበዘበዘው ማን አለ
ቤት ጓዳው ያልተመሰቃቀለ
ተርታውን ከደጃፍ እደጃፍ
ነጣቂው ነጠቀ ከቶ አንድም ሳያልፍ
አዝማች · Chorus
ከሰፈር ሰፈር
ውጭ ጉዋሮው ሳየቀር
ከበራፍ በራፍ
ከቶ አንድም ቤት ሳታልፍ
አጽናኝ መንፈስ ሆይ ፈጥነህ ድረስ ለእኛ
ቁጥር 3 · Verse 3
የምንወዳቸው ተለይተው ከኛ
እስከመቼ ድረስ ሆነን ሃዘንተኛ
ህጻናት ተጣለ ባዶ ቤት
እናት አባት አልቀው በቅጽበት
ሽማግሌዎች ጡዋሪም የላቸው
ተቀጭተው ተስፋ ልጆቻቸው
የፍራቻ ጥላ የሥጋት
ሰንብቶአል ምድሪቱን ከዋጣት
ጠዋት ያዩት በሕይወት ለማታ
በነበር ይወሳል በቅጽበት በአንዳፍታ
አዝማች · Chorus
ከሰፈር ሰፈር
ውጭ ጉዋሮው ሳየቀር
ከበራፍ በራፍ
ከቶ አንድም ቤት ሳታልፍ
አጽናኝ መንፈስ ሆይ ፈጥነህ ድረስ ለእኛ
ቁጥር 4 · Verse 4
የምንወዳቸው ተለይተው ከኛ
እስከመቼ ድረስ ሆነን ሃዘንተኛ
ምናልባት ብትራራ ጌታችን
የእንጨት ርብራብ ሆኗአል ቤታችን
አሳር ነው ዞሮም መግባቱ
አባዜው ክፍ ሆኖ የቤቱ
ያልፋል ይህ የከፍ ቀን
እግዚአብሔር በምረት ሲያውቀን
ስብራት ይጠገንና
የዓይናችን እንባ ፍፁም ይደርቅና
የትናንት ወሬ ይሆንና
ይሞላል ሰው በምሥጋና
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ