መርምር ሩጫዬን
Mermer Ruchayien
2010 · ትራክ 6 · አማርኛ
የቆምኩበት ስፍራ ይህ ግዑዙ መሬት ግዑዙ መሬት
የሰላም ነው የደም ጠብ የበቀለበት ጠብ የበቀለበት
የእርምጃዬ ማብቂያ የእግሮቸን አቅጣጫ የእግሮቸን አቅጣጫ
መርምር ሩጫዬን የሕይወቴን ምርጫ የሕይወቴን ምርጫ
የሕይወቴን ምርጫ የሕይወቴን ምርጫ
ልቤን ብትከፍተው ጫካኝ ነው ወይ ገራም ጫካኝ ነው ወይ ገራም
የእጆቸ መዘርጋት ለሰይፍ ነው ለሰላም ለሰይፍ ነው ለሰላም
ሌሊት በምንጣፌ በጭርታው ሰዓት በጭርታው ሰዓት
የማውጠነጥነው የአዕምሮዬ ሙላት የአዕምሮዬ ሙላት
የአዕምሮዬ ሙላት የአዕምሮዬ ሙላት
ከአንተ (፫ጊዜ) ምን የደበቃል
ፍጥረት እርቃኑን ነው ግልጥልጥ ብሏል
ድልድል ቢሆን ወይ ገደላማ
በራ ቢሆን ወይ ደመናማ
እዚህ በቅርብ ወይ እዚያ በሩቅ
ደረቅ መሬት ቢሆን ወይ ውኃ ጥልቅ
በምድር በታች በአየር በላይ
የሚያልፍህ የለም ዓይንህ ሳያይ
ከአንተ (፫ጊዜ) ምን የደበቃል
ዓይኖቼ ተከፍተው ወዴት አማተሩ ወዴት አማተሩ
የምላሴ ቅምሻ ጣፋጭ ነው መራሩ ጣፋጭ ነው መራሩ
ቃሌ የአንደበቴ የሚወረወረው የሚወረወረው
ለጐረቤት ጆሮ በራድ ወይ እሳት ነው በራድ ወይ እሳት ነው
በራድ ወይ እሳት ነው በራድ ወይ እሳት ነው
የፊቴ ገታ ውጫዊ ምስሌ ውጫዊ ምስሌ
ላየኝ በሩቅ መሳይ ሁሉን መደለሌ ሁሉን መደለሌ
ከብላቴንነት ከቶ መች ጠቀመኝ ከቶ መች ጠቀመኝ
ውስጤን የምታይ ሆይ ዛሬ ግን መርምረኝ ዛሬ ግን መርምረኝ
ዛሬ ግን መርምረኝ ዛሬ ግን መርምረኝ
ከአንተ (፫ጊዜ) ምን የደበቃል
ፍጥረት እርቃኑን ነው ግልጥልጥ ብሏል
ድልድል ቢሆን ገደላማ
ብራ ቡሆን ወይ ደመናማ
እዚህ በቅርብ ወይ እዚያ በሩቅ
ደረቅ መሬት ወይ ውኃ ጥልቅ
በምድር በታች በአየር በላይ
የሚያልፍ የለም ዓይንህ ሳያይ
ከአንተ (፫ጊዜ) ምን የደበቃል
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ