የአምልኮ ነጻነት
Yeamleko Netsanet
2010 · ትራክ 2 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
የነጻነት መዘዝ የአምልኮ ነጻነት
በበጐቹ መግቢያ ትኩሎች ዘው አሉበት
ሥርዓት የሌለበት ገደብ የሌለበት
የኢየሱስ ሥም ለንግድ ጨረታ የወጣበት
ቁጥር 2 · Verse 2
አወይ ነጻነት ፤ አወይ ነጻነት ፤ አወይ ነጻነት
ለአምልኮ ነጻነት ሱባኤ ተገብቶ
መሰደድም ቀረ ከላይ ትዕዛዝ ወጥቶ
መግቢያ በሩ ሰፋ ሰው ተግተለተለ
እንክርዳዱ ስንዴ ተኩላው በግ መሰለ
ቁጥር 3 · Verse 3
የድል አጥቢያ አርበኛ ዘለቀ ሆ ብሎ
ውጪያዊ ምስሉን ወጉን አስተካክሎ
በየጓዳው ፈላ ቤተክርስቲያን ሰሪ
ራሱ ፈላጭ ቆራጭ ባለሚኒስትሪ
ዶክትሪኑ በዛ መድረክ ጠበበ
ጥራት ሳይሆን ብዛት ስንቱን ሰበሰበ
ግርግር እንዳይሉት ወይ ዘመነ ጥፉ
የአምልኮ ነጻነት ብለውት አረፉ
አዝማች · Chorus
ኦሆ ኦሆ ነጻነት
ነጻነት እያሉ
ሲያሞግሱሽ ዋሉ
ጉድሽ ግን ብዛቱ
ቁጥር 4 · Verse 4
ላወቀው ለስንቱ
የነጻነት መዘዝ የአምልኮ ነጻነት
በበጐቹ መግቢያ ትኩሎች ዘው አሉበት
ሥርዓት የሌለበት ገደብ የሌለበት
የኢየሱስ ሥም ለንግድ ጨረታ የወጣበት
አወይ ነጻነት ፤ አወይ ነጻነት ፤ አወይ ነጻነት
ቁጥር 5 · Verse 5
መጽሃፍ ቅዱስ ኮሌጅ አጠናቅቄያለሁ
ምስክር ወረቀት ቆቤንም ጭኛለሁ
አንግዲህ የቀረኝ ሀያ ሰው ሰብስቤ
ኪሳቸው ኪሴ ነው ለወጭ ለቀለቤ
እያሉ የሚያልሙ ወንጌል ተጡዋሪዎች
ዙሪያችን ፈልተዋል ሥራ ጠላቱዎች (፪x)
ቀላዋጮች ብዙ ተንባዮች ለእንጐቻ
መረቅ ላጠጣቸው ላበላቸው ብቻ
እንደ መተተኛ እዚህ እዛ እያሉ
ቅልጥም ላገኙበት ይተነብያሉ
የነጻነት ውልዶች ስንቱን ያሞኛሉ
በግርግር መጥተው የተቀላቀሉ የተቀላቀሉ
አዝማች · Chorus
ኦሆ ኦሆ ነጻነት
ነጻነት እያሉ
ሲያሞግሱሽ ዋሉ
ጉድሽ ግን ብዛቱ
ቁጥር 6 · Verse 6
ላወቀው ለስንቱ
የነጻነት መዘዝ የአምልኮ ነጻነት
በበጐቹ መግቢያ ትኩሎች ዘው አሉበት
ሥርዓት የሌለበት ገደብ የሌለበት
የኢየሱስ ሥም ለንግድ ጨረታ የወጣበት
አወይ ነጻነት ፤ አወይ ነጻነት ፤ አወይ ነጻነት
ቁጥር 7 · Verse 7
ራሱን የሚያዳንቅ አገልጋይ ሞልቶናል
ሥሙን ሲያስተዋውቅ ፎቶውን አይተናል
ስብከቴ ነክቶአቸው እልፍ ሰዎች ዳኑ
አጋንንቶች ወጡ ብሎ ማጋነኑ
ራሱ እንዳደረገው በኃይል በጥበቡ
እውቁልኝ ብሎ ሥሙን ማነብነቡ (፪x)
ባለድርጂቱስ በጐ አድራጊ መሳይ
በሙት ልጆች ነጋጅ ጫና ጫንቃቸው ላይ
በድሀ ሥም ዞሮ ባከማቸው ሁሉ
ፎቁን ገንብቶበት የሚታይ ለሁሉ
ምናልባት ሲተርፈው ከርሱን ካጠገበ
ትርፍራፊው ሲቀር ድሆቹን አሰበ
አዝማች · Chorus
ኦሆ ኦሆ ነጻነት
ነጻነት እያሉ
ሲያሞግሱሽ ዋሉ
ጉድሽ ግን ብዛቱ
ቁጥር 8 · Verse 8
ላወቀው ለስንቱ ፤ ላወቀው ለስንቱ (፪x)
ጉድሽ ግን ብዛቱ
ላወቀው ለስንቱ ፤ ላወቀው ለስንቱ (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ