እኔ የማመልከው
Enie Yemamelkew
2005 · ትራክ 6 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
የጌታን ውለታ በምን እመልሳለሁ
ዘላለም ላመልከው ቃል ገብቻለሁ
የአምላኬን ውለታ በምን እመልሳለሁ
ዘላለም ላመልከው ቃል ገብቻለሁ
ችግረኛን የሚታደግ የቆሰለን የሚፈውስ
ለታመነው ፈጥኖ የሚደርስ ሥሙ ጌታ ኢየሱስ
ማዕበሉን አሳለፈኝ ወጀቡንም አሻገረን
እጄን ይዞ እየመራ እዚህ አደረሰኝ
አዝማች · Chorus
እኔ የማመልከው ጌታዬ
አባት ወንድም ጓደኛዬ የጸና ስሙ መሸሸግያዬ
ቁጥር 2 · Verse 2
በፍቅሩ ተማርኬያለሁ ፍቅጄ አመልከዋለሁ
ለዘላለም ለእርሱ እገዛለሁ (፪x)
ያን ፈተና የገነነ እንደተራራ የሆነ
የአምላኬን ስም ስጠራበት እንደ ጉም ተነነ
የባሕሩም ወጀብ ከብዶ ነፍሴን በሌት አስጨንቋት
ግን ጌታዬ ምን ተስኖት ተረማመደበት
አዝማች · Chorus
እኔ የማመልከው ጌታዬ
አባት ወንድም ጓደኛዬ የጸና ስሙ መሸሸግያዬ
ቁጥር 3 · Verse 3
በፍቅሩ ተማርኬያለሁ ፈቅጄ አመልከዋለሁ
ለዘላለም ለእርሱ እገዛለሁ (፪x)
የጌታን ውለታ በምን እመልሳለሁ
ዘላለም ላመልከው ቃል ገብቻለሁ
የአምላኬን ውለታ በምን እመልሳለሁ
ዘላለም ላመልከው ቃል ገብቻለሁ
እግዚአብሔር እረኛዬ የማይተኛ ጠባቂዬ
በክፉ ቀን ማምለጫዬ ሥሙ መከታዬ
ይመራኛል አምነዋለሁ እርሱ ይግዛኝ እገዛለሁ
እንደ እግዚአብሔር መልካም አባት ወዴት አገኛለሁ
አዝማች · Chorus
እኔ የማመልከው ጌታዬ
አባት ወንድም ጓደኛዬ የጸና ስሙ መሸሸግያዬ
ቁጥር 4 · Verse 4
በፍቅሩ ተማርኬያለሁ ፍቅጄ አመልከዋለሁ
ለዘላለም ለእርሱ እገዛለሁ (፬x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ