Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ክብር ለኢየሱስ

Kibir LeEyesus

2005 · ትራክ 11 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ለጻድቁ ክብር ክብር ይሁን

የሚል ዝማሬ ከምድር ዳር ሲሰማ

እኔም ድምፄን አብሬ አነሳለሁ

ለእግዚአብሔር ክብር እዘምራለሁ

ቅዱሳን መላዕክቱ ባንድነት

ሌሊትና ቀንም ሚሰግዱለት

የምድር ፍጥረታት ጉዑዛን ሁሉ

ለቅዱሱ መንፈስ ይገዛሉ

ደሙን አፍስሷልና እኔን ሊገዛ

ለአዳኜ ኢየሱስ ምስጋናው ይብዛ (፪x)

ክብር ለእግዚአብሔር

ክብር ለኢየሱስ

ክብር ለመንፈስ ቅዱስ

ሥሙ በዓለም ይንገስ (፲፬x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ