ኢየሱስ
Eyesus
2005 · ትራክ 4 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ሥምህን ሳስጠራ በዝማሬ
በቤትህ ስኖር እስከዛሬ
አይጠገብም ከማር ይጥማል
ሥምህ ከሥሞች ሁሉ ይልቃል
ያንተን ውለታ ነፍሴ ተረድታ
ታከብርሃለች ጠዋትና ማታ
ታከብርሃለች ቀንና ማታ
ቀናት አለፉ እንደ ጥላ
አምና ካቻምና ቀረ ከኋላ
ባሳለፍኳቸው ዘመኞቼ
አፍሬ አላወቅም አንተን ጠርቼ
የጸና ክንድ ነው መሸሸጊያ
ጌታዬ ስምህ መጠለያ
ካለም ጥፋት ማምለጫ ጥላ
አዝማች · Chorus
ኢየሱስ ጌታዬ አምላኬ
እኔ ከቶ አልጠግብም ሥምህን ጠርቼ
ብዙ ምስጋናህን ዘምሬ መስክሬ
ቁጥር 2 · Verse 2
አባ አባት ብሎ ማነው ያፈረ
አንተን ተማምኖ ከስሮ የቀረ
ጻድቅ ተርቦ ዘሩ ሲለምን
በታሪክ የለም አልሰማንም
ለኔስ ማትረፍ ነው ቤትህ መኖሬ
ያንተን ምስጋና መዘመሬ
ቅዱስ ሥምህን መመስከሬ
አዝማች · Chorus
ኢየሱስ ጌታዬ አምላኬ
እኔ ከቶ አልጠግብም ሥምህን ጠርቼ
ብዙ ምስጋናህን ዘምሬ መስክሬ (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
"ኢየሱስ ሥምህ እንደሚፈስ ዘይት ነው
አጥንትን ሁሉ ዘልቆ እንደሚገባ
ነፍስንም እንደሚያረሰርስ ቁስልንም እንደሚፈውስ
መልካም መዓዛ ያለው ዘይት ነው
ለክቡር ሥምህ እዘምራለሁ"
ኢየሱስ (ኢየሱስ) ጌታዬ (ጌታዬ)
መድህኔ (መድህኔ) አመልክሃለሁ እኔ (፫x)
ሥምህ ከሥሞች ሁሉ በላይ ነው
ከስልጣን ሁሉ በላይ ስልጣን ያለው
በምስጋና ቃል እጠራሃለሁ ጠላቶቼን እረግጣለሁ (፫x)
ጌታዬ ሥምህ መሸሸጊያ
ከዓለም ጥፋት ማምለጫ ጥላ
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ