Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

መዝሙር ፺፩

Mezmur 91

2005 · ትራክ 8 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

"መዝሙር ፺፩"

“በልዑል መጠጊያ የሚኖር

ሁሉንም በሚችል አምላክ ጥላ ውስጥ ያድራል

እግዚአብሔርን አንተ መታመኝያዬ ነህ እለዋለሁ

አምላኬና መሸሸጊያዬ ነው በእርሱ እታመናለሁ "

"መዝሙር ፺፩"

በልዑል መጠጊያ የሚኖር

ሁሉንም በሚችል አምላክ ጥላ ውስጥ ያድራል

እግዚአብሔርን አንተ መታመኛዬ ነህ እለዋለሁ

አምላኬና መሸሸጊያዬ ነው በእርሱ እታመናለሁ (፪x)

ነፍሴን ከአዳኝ ወጥመድ ከአደገኛው መንገድ

ከለሊቱ ግርማ ካስፈሪው ጨለማ

በቀን ከሚበረው ከጠላት ፍላጻ

በክንፎቹ ጋርዶ ሸሽጎኛልና

በእርሱ እታመናለሁ ያስጥለኛል

ስሙን አውቀዋለሁ ይጋርደኛል

በመከራዬ ጊዜ ከእኔ ጋር ነው

ታማኙን አምላኬን ላመስግነው

ላመስግነው ላመስግነው እርሱ ታማኝ ነው (፬x)

አንዳንዴ እምነቴ ሲፈተንና ስታገል

አቋራጭ መንገድ ስፈልግ ቶሎ ልገላገል

ያን ጊዜ ይመጣና ቅዱስ ቃሉ ወደልቤ

ፈጥኖ ይመልሰኛል ካልተቀደሰው ሃሳቤ

ነፍሴን ከአዳኝ ወጥመድ ከአደገኛው መንገድ

ከለሊቱ ግርማ ካስፈሪው ጨለማ

በቀን ከሚበረው ከጠላት ፍላጻ

በክንፎቹ ጋርዶ ሸሽጎኛልና

በእርሱ እታመናለሁ ያስጥለኛል

ስሙን አውቀዋለሁ ይጋርደኛል

በመከራዬ ጊዜ ከእኔ ጋር ነው

ታማኙን አምላኬን ላመስግነው (፪x)

ክብር (፱x)

ክብር ለርሱ ይሁን (፫x) - ክብር ለርሱ ይሁን (፫x)

ክብር ለርሱ ይሁን (፫x) - ክብር ለርሱ ይሁን (፫x)

ክብር ለንጉሡ (፫x) - ክብር ለንጉሡ (፫x)

ክብር ለርሱ ይሁን (፫x) - ክብር ለርሱ ይሁን (፫x)

ክብር ለንጉሡ (፫x) - ክብር ለንጉሡ (፫x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ