የጸና ግንብ
Yetsena Ginb
2005 · ትራክ 7 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
የጸና ግንብ ነው ያንተ ሥም ጌታዬ
በመከራዬ ቀን ሆነኝ መጠጊያዬ
ጻድቅ ሥምህን ጠርቶ ከጉዳት ያመልጣል
ካስፈሪው ጨለማ ከጉድጓድ ይወጣል
አዝማች · Chorus
ሥምህ ይክበር አባቴ ሥምህ ይክበር መድኃኒቴ
ቁጥር 2 · Verse 2
ሥምህ ይክበር አባቴ ሥምህ ይክበር መድኃኒቴ መድኃኒቴ (፪x)
ሥምህ ከሥም ሁሉ በላይ ነው አምላኬ
ፈጥነህ ትደርሳለህ ስጮህ ተንበርክኬ
ከጨካኙ አውሬ ከሞት ኃይል ያድናል
የሥምህ ጉልበቱ ጠላቴን ይጥላል
አዝማች · Chorus
ሥምህ ይክበር አባቴ ሥምህ ይክበር መድኃኒቴ
ቁጥር 3 · Verse 3
ሥምህ ይክበር አባቴ ሥምህ ይክበር መድኃኒቴ መድኃኒቴ (፪x)
ብዙዎች ተነሱ በኃይል የገነኑ
ዝናቸው የናኘ ላፍታ ለሰሞኑ
ዝንታለም አልቆዩም እንደጥላ አልፈዋል
የኔ ጌታዬ ሥም ዛሬም ድንቅ ይሰራል
አዝማች · Chorus
ሥምህ ይክበር አባቴ ሥምህ ይክበር መድኃኒቴ
ቁጥር 4 · Verse 4
ሥምህ ይክበር አባቴ ሥምህ ይክበር መድኃኒቴ
ወደ ኃይሉ ችሎት ገባሁ ያለከልካይ
አጋፋሪ አልቆመ ዘበኛ ደጁ ላይ
በጨነቀኝ ጊዜ በየትኛውም ቦታ
ፊቱ አፈሳለሁ የእንባዬን ጠብታ
የልቤን ብሶት ያያል ጩኸቴንም ያዳምጣል
እንባዬን ያብስልኛል እንደንስር ያድሰኛል
የጸና ግንብ ነው ያንተ ስም ጌታዬ
በመከራዬ ቀን ሆነኝ መጠጊያዬ
ጻድቅ ስምህን ጠርቶ ከጉዳት ያመልጣል
ካስፈሪው ጨለማ ከጉድጓድ ይወጣል
አዝማች · Chorus
ሥምህ ይክበር አባቴ ሥምህ ይክበር መድኃኒቴ
ቁጥር 5 · Verse 5
ሥምህ ይክበር አባቴ ሥምህ ይክበር መድኃኒቴ መድኃኒቴ (፪x)
ሥምህን ሳነሳሳ ሰይጣን ይሸበራል
ባንድ መንገድ መጥቶ በብዙ ይሸሻል
በተኩላና በእባቡ ላይ እጫማለሁ
አንበሳ ዘንዶውን እረጋግጣለሁ
በጌታ እታመናለሁ ሥሙንም አውቀዋለሁ
ስጠራው ይመልስልኛል ማዳኑንም ያሳየኛል ያከብረኛል (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ