መዝጊያ
Outro
2005 · ትራክ 12 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
አንተን ጠርቶ ማን አፈረ
ተማምኖብህ ማን ከሰረ
የተዘጋን ትከፍታለህ
የታሰረን ትፈታለህ
የታመመን ታድናለህ
የሞተውን ታስነሳለህ
ስልጣን የአንተ ጌታዬ ሆት ስልጣን የአንተ
ስልጣን የአንተ የኔ ጌታ ስልጣን የአንተ
ስልጣን የአንተ ጌታዬ ሆይ ስልጣን የአንተ
የፈጠረን በረሃ በሌለበት ውሃ
በምድረበዳ ለተጐዳ
ዘመድ ለሆነው ባዳ እንደ ማለዳ
አምቆ ሚስጥሩን በልቡ ጓዳ
እንባውን የጻፈ በጸሎት ሰሌዳ
ለቆዘመው ብቸኛ ለሌለው ጓደኛ
ሃሩር ላከሰለው መንገደኛ
የሚቀምሰው ላጣ ረሃብተኛ
በሀገር በምድሩ ስደተኛ
በወገኑ መሃል መጻተኛ
ድሃ ችግረኛ የሆነም እንደኛ
ለሚሻህ ቅን ፈራጅ ዳኛ
ከቤቱ ሳይወጣ መናን የሚሻ
ለነፍሱ አጽናኝ ደራሽ አዛኝ ለስብራቱ ጠጋኝ
በሩን ዘግቶ ለሚያለቅሰው
ነገር ከብዶት ሆድ ለባሰው
አጥቶ እንባውን የሚያብሰው
ረድኤት የሚሆነው ከሰው
ማነው የሚደርሰው
ጌታ ነው ኢየሱስ ጌታ ነው (፭x)
ለብቸና ተጓዥ መንገደኛ
የፍቅር አምላክ እውነተኛ
ፍቅር ማነው እግዚአብሔር ነው
ፍቅር ማነው ኢየሱስ ነው
ኃጢአት አሸፍቶት ጫካ የገባውን
ጸጋውን ተገፎ የተራቆተውን
የበደሉን ብዛት መሸከም ላቃተው
ነገር ግራ ገብቶት ለሚወተውተው
የእዬዬ ኑሮ የለቅሶ ሸለቆ
የጨከነ ውጋት ሃዘናትን ዘልቆ
በጦርነት ሜዳ ፍልሚያ መሃል ወድቆ
ፈገግታ ከፊቱ ከቤቱ ሳቅ ርቆ
እንባው ካይኑ ደርቆ
ሃዘን ኑሮ ሲከፋ
ረዳት ወገን ሲጠፋ
ወጀብ አውሎ ሲከፋ
የመከራ ጉም ሲያካፋ
መስቀሉ ስር ሲደፋ
ጌታ ኢየሱስ ደርሶ እንባውን አብሶ
የጽድቅ ልብስ አልብሶ አሮጌን አድሶ
በፍቅሩ እጁ ዳሶ በደሌን ደምስሶ
አጥቦና ቀድሶ ፈውሶ
በክብር ያቆማል ጥያቄን መልሶ
ጌታ ነው ኢየሱስ ጌታ ነው (፭x)
አዝማች · Chorus
አንተን ጠርቶ ማን አፈረ
ተማምኖብህ ማን ከሰረ
የተዘጋን ትከፍታለህ
የታሰረን ትፈታለህ
የታመመን ታድናለህ
የሞተውን ታስነሳለህ
ስልጣን የአንተ ጌታዬ ሆት ስልጣን የአንተ
ስልጣን የአንተ የኔ ጌታ ስልጣን የአንተ
ስልጣን የአንተ ጌታዬ ሆይ ስልጣን የአንተ
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ