እንመርቃቹሃለን
Enmereqachuhalen
ትራክ 9 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
በስመአብ ወወልድ ወመፈስ ቅዱስ አንድ አምላክ
ይሄ ጋብቻ የተባረከ ጋብቻ ይሁንልን አሜን
አዝማች · Chorus
አዲስ ኑሮ አዲስ ቤት አሃዱ የተባለው ዛሬ
በመልካም እንዲዘልቅ ይህ የፍቅር ጅማሬ
እንመርቃቹሃለን አሜን (፮x)
በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ
ተባረኩ ብለን እንመርቃቹሃለን (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ክርስቶስ እርሱ የሆነው መሰረት
እራስ ሆኖ ይንገሥበት እዚህ ይግባልን??? ቸርነት
ትዳሩም በመንፈስ ቅዱስ ተመርቶ
የባርኮት ሽታ ሸቶ በምሳሌነት ተሞልቶ
ከድግስ ያለፈ (አዎ) በሕይወታቸው ጉዞ (አዎ)
ይምራቹህ እጃችሁን ይዞ
አዝማች · Chorus
አዲስ ኑሮ አዲስ ቤት አሃዱ የተባለው ዛሬ
በመልካም እንዲዘልቅ ይህ የፍቅር ጅማሬ
እንመርቃቹሃለን አሜን (፮x)
በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ
ተባረኩ ብለን እንመርቃቹሃለን (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
ቤተሰብ ጤናማ ቤተክርስቲያን
ያድርጋት እንደብርሃን በፀጋው ብዛት ለማዳን
የደስታ ምንጭ ሆኖ ይፍለቅለቅበት
የተጠሙም የሚረኩበት ያዘኑም የሚደሰቱበት
እግዚአብሔር አዘዘ (አዎ) ጋብቻ እንዲከበር (አዎ)
ከጥንቱም ልክ እንደዚህ ነበር
ቃልኪዳን አላቹህና ከእግዚአብሔር
ብዙ ተባዙ ተባልን የአምላካቹህ ባርኮት ነው
ውለዱ ክበዱ ይሁን ደስታ
በፍቅር አምላክ በጌታ በሕይወታችሁ አለኝታ
እግዚአብሔር ያኖራል (አዎ) መኖሪያቹህ ሆኖ (አዎ)
ማን አፍሯል በእርሱ ተማምኖ
አዝማች · Chorus
አዲስ ኑሮ አዲስ ቤት አሃዱ የተባለው ዛሬ
በመልካም እንዲዘልቅ ይህ የፍቅር ጅማሬ
እንመርቃቹሃለን አሜን (፮x)
በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ
ተባረኩ ብለን እንመርቃቹሃለን (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ