ምሥጋና ለእግዚአብሔር
Mesgana LeEgziabhier
ትራክ 7 · 4:02 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
ምሥጋና ለእግዚአብሔር ምሥጋና ፤ ምሥጋና
ሁለቱን ሙሽሮች አንድ አድርጓልና ፤ ምሥጋና (፪x)
ቁጥር 1 · Verse 1
የደስታ ቀን ነው ዛሬ
የድል ቀን ነው የዝማሬ
እግዚአብሔር ስለረዳቸው
ኑሮም መሰረተላቸው
የፍቅርን ቤት ሰራላቸው
ባሳለፉት ዘመናቸው
መከራ እንኳን ቢገጥማቸው
በዚያ ሁሉ አግዟቸው
ከክፉ ሃሳብ ጠብቋቸው
ዛሬ ለዚህ አበቃቸው
አዝማች · Chorus
ምሥጋና ለእግዚአብሔር ምሥጋና ፤ ምሥጋና
ሁለቱን ሙሽሮች አንድ አድርጓልና ፤ ምሥጋና (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
በሶስትም የተገመደ አይበጠስ አይበጠስ
ጌታ እስካለ ድረስ (፬x)
ተከናወነ ብቸኝነት ቀረ
ጌታ ያስደስታል እያጣመረ እያስተሳሰረ (፪x)
አሃሃ ፊታቸው አሃሃ አላፈረም
አሃሃ ጋብቻው አሃሃ ስመረ (፰x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ