Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ምክር

Meker

ትራክ 3 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ከጉብዝናህ ሚስትህ ጋር ደስ ይበልህ አዎ ደስ ይበልህ

ውደዳት አፍቅራት እርሷን እንደራስህ

እህትህም ሚስትህም ባልንጀራህም ነች

እረዳትህ ሆና ለአንተ የተሰጠች (፪x)

በረከት ካገኘ ሚስትን ያገኘ ሰው

ከእግዚአብሔርም ዘንድ ሞገስ ከተሰጠ

እያመሰገነ ስለዚህ ስጦታ

ቤቱን በጽድቅ ይምራ ይንከባከባታል (፪x)

የቃልኪዳን ተጋቢዎች እናንተን ያጣመረ

በመሃከላቹህ እግዚአብሔር አለ

በመሃከላቹህ እግዚአብሔር አለ

በመሃከላቹህ ምስክር እርሱ አለ

በመሃከላቹህ ምስክር እርሱ አለ (፪x)

እድምተኛ አይደለም በልቶና ጠጥቶ

እንደሚሸኝ ወዳጅ ለእናንተው ትቶ

ያስጀመረ ጌታ አብሯቹህ ይዘልቃል

ብቻ አባት ሆይ በሉት ቤቱ ቤት ይሆናል (፪x)

አስተዋይ ሚስት ግን ከእግዚአብሔር ዘንድ ናት

በእግዚአብሔር ቃል ላይ እንደተባለላት

ለጌታ ለኢየሱስ እንደምትገዢ

ለባልሽም ደግሞ እንዲሁ ተገዢ (፪x)

ልባም ሴት ለባሏ ዘውድ እንደምትሆነው

ክብሩ የት እንዳለ ቃሉ ካጸደቀው

ማፈሪያህ እንዳይሆን አንቺም እንዲህ ሁኚ

ግን ልባምነትን ከቃሉ አግኚ (፪x)

የቃልኪዳን ተጋቢዎች እናንተን ያጣመረ

በመሃከላቹህ እግዚአብሔር አለ

በመሃከላቹህ እግዚአብሔር አለ

በመሃከላቹህ ምስክር እርሱ አለ

በመሃከላቹህ ምስክር እርሱ አለ (፪x)

እድምተኛ አይደለም በልቶና ጠጥቶ

እንደሚሸኝ ወዳጅ ለእናንተው ትቶ

ያስጀመረ ጌታ አብሯቹህ ይዘልቃል

ብቻ አባት ሆይ በሉት ቤቱ ቤት ይሆናል (፪x)

የብልህ ቤት ይሁን ክርስቶስ ራስ ሆኖ

ዐይንም በእርሱ አድርጐ በስሙ ተማምኖ

መንገዱን ዝለቁት የኑሮን ጐዳና

ግልጽ ሁኑ ሁሉን ነገር ተከባበሩና (፪x)

ዕውቀትን እንደዘውድ በላያቹህ ጫኑ

ጥበብን እንዳትዉ ሞኞች እንዳትሆኑ

በፍቅር ለጸና ለተቻቻለ ሰው

ጋብቻ ክቡር ነው መኝታው ንጹህ ነው (፪x)

የቃልኪዳን ተጋቢዎች እናንተን ያጣመረ

በመሃከላቹህ እግዚአብሔር አለ

በመሃከላቹህ እግዚአብሔር አለ

በመሃከላቹህ ምስክር እርሱ አለ

በመሃከላቹህ ምስክር እርሱ አለ (፪x)

እድምተኛ አይደለም በልቶና ጠጥቶ

እንደሚሸኝ ወዳጅ ለእናንተው ትቶ

ያስጀመረ ጌታ አብሯቹህ ይዘልቃል

ብቻ አባት ሆይ በሉት ቤቱ ቤት ይሆናል (፪x)

እግዚአብሔር አለ (፬x) ፤ እግዚአብሔር አለ (፬x)

እግዚአብሔር አለ (፬x) ፤ እግዚአብሔር አለ (፬x)

እግዚአብሔር አለ (፬x) ፤ እግዚአብሔር አለ (፬x)

እግዚአብሔር አለ (፬x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ