እንዲህ አይነቷ ናት
Endih Aynetwa Nat
ትራክ 4 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ልባምን ሴት ማን ሊያገኛት ይችላል
ከእግዚአብሔር ቃል ካልሆነ ከየት ይገኛል
ከዝርግፍ ጌጥ ይልቅ ውስጧ የበለጠ
በፀጋው መንፈሷ ሁሉ ያጌጠ
ወርቅ አያምራት እርሷ ራሷ ወርቅ ናት
ለይሉኝታ ምታስመጣው ጥሎሽ የላት
መልካም አእምሮ የበሰለ ባህሪ
ከሁሉም በላይ እግዚአብሔርን ፈሪ
አዝማች · Chorus
እንዲህ አይነቷ ናት (፫x) እውነተኛ ረዳት
እንዲህ አይነቷ ናት (፫x) እውነተኛ ረዳት
ቁጥር 2 · Verse 2
ከውጭ ውበት የውስጥ ውበቷ በልጧል
አካሄዷ ንግግሯ ይገልጣል
ማስተዋሏ ዕውቀቷ የበዛ ነው
የማመዛዘን ችሎታ ሁሉ ያለው (በጣም)
እንደ ሰነፍ ሴቶች አትናገርም
በመከራም ውስጥ ተስፋን አትቆርጥም
ከአጥንቱ ነው እርሷ የተሰራችው
ለዚህ ነው ሁሉን ነገር የቻለችው
አዝማች · Chorus
እንዲህ አይነቷ ናት (፫x) እውነተኛ ረዳት
እንዲህ አይነቷ ናት (፫x) እውነተኛ ረዳት
ቁጥር 3 · Verse 3
የባሏም ልብ ይተማመንባታል
እውነተኛው ፍቅር ይመግባታል
ትገዛለች ለቃሉ ለሃሳቡ
በግድ ሳይሆን አሸንፏት ፍቅሩ
ተወስና እርሷ ለእርሱ ተሰጥታ
በሌላ ወንድ ልቧም ሳያመነታ
አንድ ለአንድ አይደለም የእርሷ ሂሳብ
እንደቃሉ አንድ ናት ያለ ሃሳብ
አዝማች · Chorus
እንዲህ አይነቷ ናት (፫x) እውነተኛ ረዳት
እንዲህ አይነቷ ናት (፫x) እውነተኛ ረዳት
ቁጥር 4 · Verse 4
ገና ሌሊት በማለዳ ተነስታ (እንዲህ አይነቷ ናት)
ምግብ ለቤቷ ሰዎች ሁሉ ሰርታ (እንዲህ አይነቷ ናት)
ወገቧን በመቀነቷ ታጥቃለች (እንዲህ አይነቷ ናት)
ስራዋን በጊዜው ትጨርሳለች (እንዲህ አይነቷ)
እንድትለፋ አይደለም እርሱ ያገባት (እንዲህ አይነቷ)
እረዳት ናት ሁሉም ነገር የገባት (እንዲህ አይነቷ ናት)
ሰራተኛው አይደለችም ለቤቱ (እንዲህ አይነቷ ናት)
ናት ለባሏ ድምቀቱ ውበቱ (እንዲህ አይነቷ)
አዝማች · Chorus
እንዲህ አይነቷ ናት (፫x) እውነተኛ ረዳት
እንዲህ አይነቷ ናት (፫x) እውነተኛ ረዳት
ቁጥር 5 · Verse 5
ውበት ሃሰት ነው ደምግባትም (ከንቱ ነው)
ውበት ሃሰት ነው ደምግባትም (ከንቱ)
እግዚአብሔርን የምትፈራ ሴት እርሷ ትመሰገናለች (ትመሰገናለች)
እግዚአብሔርን የምትፈራ ሴት እርሷ ትመሰገናለች (እርሷ) (፪x)
እግዚአብሔርን የምትፈራ ሴት እርሷ ትመሰገናለች (፪x)
አዝማች · Chorus
እንዲህ አይነቷ ናት (፬x) እውነተኛ ረዳት
እንዲህ አይነቷ ናት (፬x) እውነተኛ ረዳት
ቁጥር 6 · Verse 6
እንዲህ አይነቷ ናት (፬x) እውነተኛ ረዳት
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ