ሙሽሪት ሙሸራው
Musherit Musheraw
ትራክ 6 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ሙሽሪት ሙሽራው እንኳን ደስ አላችሁ
ቁጥር 2 · Verse 2
የቃልኪዳን አምላክ ያስተሳሰራቹህ
እግዚአብሔር ነውና የትዳር ጅማሬ
ኦ ስራው ግሩም ነው
ደስ ብሎናል ዛሬ
(አሜን) ልዑል አሰናዳ ፤ (አሜን) ባርኮት የሚበላ
(አሜን) ከማመስገን በቀር ፤ (አሜን) ምን ይባላል ሌላ
(አሜን) የዘለዓለም አምላክ ፤ (አሜን) ወደ እረፍት አመጣን
(አሜን) ከብቸኝነቱ ፤ (አሜን) መንደር እያወጣ
አዝማች · Chorus
ሙሽሪት ሙሽራው እንኳን ደስ አላቹህ
የቃልኪዳን አምላክ ያስተሳሰራቹህ
እግዚአብሔር ነውና የትዳር ጅማሬ
ኦ ስራው ግሩም ነው
ደስ ብሎናል ዛሬ
ቁጥር 3 · Verse 3
(አሜን) አክሊል የለበሰ ፤ (አሜን) ሙሽራው ሲያምርበት
(አሜን) በጌጥ ሽልማቷ ፤ (አሜን) ሙሽሪት ሲያምርባት
(አሜን) ነገር ግን እግዚአብሔር ፤ (አሜን) ጽድቅን አጐናጽፎ
(አሜን) ሰውን ለዚህ ያበቃል ፤ (አሜን) ሁሉን አሳልፎ
አዝማች · Chorus
ሙሽሪት ሙሽራው እንኳን ደስ አላቹህ
የቃልኪዳን አምላክ ያስተሳሰራቹህ
እግዚአብሔር ነውና የትዳር ጅማሬ
ኦ ስራው ግሩም ነው
ደስ ብሎናል ዛሬ
ቁጥር 4 · Verse 4
አዲስ ጐጆ ወጪ በይ ባርኮቱን ጠጪ
ብሎ የመረቃት ደጉ ቸሩ አባት
እረድቷት አምላኳ ሲለወጥ ታሪኳ
ጐጆን ማን አስወጣት ጌታ ነው ያገዛት (፪x)
ምህረቱ ብዙ ነው ምህረቱ የጌታ
በእርሱ ተጀምሯል የሙሽሪት ቤቷ (፬x)
አዲስ ስፍራ ሰጥቶ በኑሮም ገብቶ
ጌታ አደላደለው ተመስገን አስባለው
ይህን ሁሉ ነገር ስላሳየን ይክበር
ቃሉን ላላጠፈው ምሥጋናችን ይሄው (፪x)
ምህረቱ ብዙ ነው የእግዚአብሔር ምህረቱ
በእርሱ ተጀምሯል የሙሽራው ቤቱ (፬x)
(አሜን) ፍቅር ግን እስከሞት ፤ (አሜን) ብርቱ ስለሆነ
(አሜን) እርሷም ለእርሱ ሆነች ፤ (አሜን) እርሱም ለእርሷ ሆነ
(አሜን) ጌታ ያነደደውን ፤ (አሜን) የፍቅርን እሳት
(አሜን) ብዙ የጥፋት ውኃ ፤ (አሜን) አይችልም ሊያጠፋት
አዝማች · Chorus
ሙሽሪት ሙሽራው እንኳን ደስ አላቹህ
የቃልኪዳን አምላክ ያስተሳሰራቹህ
እግዚአብሔር ነውና የትዳር ጅማሬ
ኦ ስራው ግሩም ነው
ደስ ብሎናል ዛሬ
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ