አብሬ ጨመሬ
Aberie Chemerie
ትራክ 2 · 6:42 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
እኔም ይህን ጌታ ላክብረው
ቁጥር 2 · Verse 2
ላክብረው ከእነርሱ ጋር አብሬ
አብሬ ምሥጋናን ጨምሬ
አብሬ ዕልልታን ጨምሬ
አብሬ አምልኮን ጨምሬ
አብሬ ጭብጨባን ጨምሬ (፪x)
አላማሩም ወይ ዛሬ ፤ አላማሩም ወይ (፪x)
እውነት የሆናቸው ጌታ አይደለም ወይ (፪x)
ሞገስ የሆናቸው ኢየሱስ አይደለም ወይ (፪x)
አላማሩም ወይ ዛሬ ፤ አላማሩም ወይ (፪x)
በስራና በቃል ብርቱ የሆነው ጌታ
እጃቸውን ይዞ ሁሌ እያበረታ
ለዚህ ላበቃቸው ስንቱን እየመታ
እዚህ አደረሳቸው ክፉን እየመታ
ቃል የገቡት ቤተሰቦቹ (፫x)
ከሁሉም ሚበልጥ አግኝቷል እጁ (፫x)
ቃል የገቧት ቤተሰቦቿ (፫x)
ወሰነች ልትኖር ከባሏ ብቻ (፫x)
ቤተሰብ ጓደኛ ዘመድ አዝማድ ሁሉ
በሰርጉ ያላችሁ ተጋባዥ በሙሉ
ላጤነት አብቅቶ ብቸኝነታቹህ
በቃ ለቀው ሄዱ ከቀድሞ ቀያቸው
አመስግኑ (ኦሆ) አጨብጭቡ (አሃ)
ለአምላካችሁ (ኦሆ) እልል በሉ (አሃ) (፪x)
አዝማች · Chorus
እኔም ይህን ጌታ ላክብረው/ላንግሰው
ላክብረው/ላንግሰው ከእነርሱ ጋር አብሬ
አብሬ ምሥጋናን ጨምሬ
አብሬ ዕልልታን ጨምሬ
አብሬ አምልኮን ጨምሬ
አብሬ ጭብጨባን ጨምሬ (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
ከመጀመሪያው (፫x)
እግዚአብሔር አንድን ወንድ ለአንድ ሴት አድርጐ ሰራው (፬x)
ከመጀመሪያው (፫x)
እግዚአብሔር አንድን ሴት ለአንድ ወንድ አድርጐ ሰራት (፬x)
ይህ ነው የእግዚአብሔር ፈቃድ ዛሬም ይህ ነው (፬x)
ይህ ነው የእግዚአብሔር ፈቃድ ዛሬም ይህ ነው (፬x)
አላማሩም ወይ ዛሬ ፤ አላማሩም ወይ (፪x)
በስራና በቃል ብርቱ የሆነው ጌታ
ሁሉን አሳመረ እጁ አለበት
ይሄው አሳመረው ቃሉ አለበታ
የቃል ኪዳን አምላክ ክንዱ አለበት
አላማሩም ወይ ዛሬ ፤ አላማሩም ወይ (፪x)
እርሱ ያገናኘውን ሰው አይለየውማ
ማጣመር ለሚችል ከፍ ይበል በዜማ
ሰው ማድረግ ለሚችል ምሥጋናን ላሰማ
መባረክ ለሚችል ዕልልታን ላሰማ
ቃል የገቡት ቤተሰቦቹ (፫x)
ከሁሉም ሚበልጥ አግኝቷል እጁ (፫x)
ቃል የገቧት ቤተሰቦቿ (፫x)
ወሰነች ልትኖር ከባሏ ብቻ (፫x)
ቤተሰብ ጓደኛ ዘመድ አዝማድ ሁሉ
በሰርጉ ያላችሁ ተጋባዥ በሙሉ
ላጤነት አብቅቶ ብቸኝነታቹህ
በቃ ለቀው ሄዱ ከቀድሞ ቀያቸው
አመስግኑ (ኦሆ) አጨብጭቡ (አሃ)
ለአምላካችሁ (ኦሆ) እልል በሉ (አሃ) (፪x)
አዝማች · Chorus
እኔም ይህን ጌታ ላክብረው/ላንግሰው
ላክብረው/ላንግሰው ከእነርሱ ጋር አብሬ
አብሬ ምሥጋናን ጨምሬ
አብሬ ዕልልታን ጨምሬ
አብሬ አምልኮን ጨምሬ
አብሬ ጭብጨባን ጨምሬ (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ