እጥላለሁ
Etilalehu
ትራክ 9 · 5:37 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
ጣል ሲለኝ እጥላለሁ ተው ሲለኝ እተዋለሁ/2
የሚረባኝን የሚያውቅልኝን ሾሜዋለው/2
ቁጥር 1 · Verse 1
መልካም ነው ያልኩት እኔ የወደድኩት
አይረባህም ሲለኝ ከእጄ ላይ ለቀቅኩት
እኔ ካሰብኩት ካወኩትም ይልቅ
አምላኬ የሚለው ይነው ውብና ድንቅ/2
አዝማች · Chorus
ጣል ሲለኝ እጥላለሁ ተው ሲለኝ እተዋለሁ/2
የሚረባኝን የሚያውቅልኝን ሾሜዋለው/2
ቁጥር 2 · Verse 2
ለአይኔ የማረኝ መብላት ያስጎመጀኝ
ሞት ስላለበት ነው እንዳትነካው ያለኝ
እኔ ላዩን እንጂ ውስጡን መች አየሁት
የዚች አለም ማማር ሞት አለው በውስጡ/2
አዝማች · Chorus
ጣል ሲለኝ እጥላለሁ ተው ሲለኝ እተዋለሁ/2
የሚረባኝን የሚያውቅልኝን ሾሜዋለው/2
ቁጥር 3 · Verse 3
ክፉውን አስጥሎ መልካም የሚሰጠው
በምክሩ ግሩም እግዚአብሔር ነው
ከኔ አስቀድሞ ስለኔ የሚያውቀው
ጌታዬን ሰምቼ ስንቴ ተርፌያለው/2
አዝማች · Chorus
ጣል ሲለኝ እጥላለሁ ተው ሲለኝ እተዋለሁ/2
የሚረባኝን የሚያውቅልኝን ሾሜዋለው/2
ቁጥር 4 · Verse 4
ሙሴን ጠራና በትሩን አስጣለው
ለካስ እባብ ነበር አቅፎት የሚዞረው
ካባቴ የወረስኩት የጥንት ነው ያልኩት
የሚናደፈወን ሸሸው አመለጥኩት/2
አዝማች · Chorus
ጣል ሲለኝ እጥላለሁ ተው ሲለኝ እተዋለሁ/2
የሚረባኝን የሚያውቅልኝን ሾሜዋለው/2
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ