Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ትመቸኛለህ

Temechegnaleh

ትራክ 7 · 9:13 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ከአንተው ጋር ልወዳጅ

ከአንተው ጋር ልስማማ (፪x)

ምን ያደርግልኛል ሌላ ሌላውማ

ምን ያደርግልኛል ሌላ ሌላውማ

ትመቸኛለህ ጌታ አሃሃ

ትመችኛለህ ኢየሱስ

ትመቸኛለህ አሃ (፪x)

ወደ ላይ ብወጣ አንተ በዚያ አለህ

ወደታች ብወድቅም ቀድመህ ትገኛለህ

ከአንተ ተሸሽቶ ወዴት ይደረሳል

ከአንተው ተስማምቶ መኖር ይሻለኛል

ከአንተው ጋር ልወዳጅ

ከአንተው ጋር ልስማማ (፪x)

ምን ያደርግልኛል ሌላ ሌላውማ

ምን ያደርግልኛል ሌላ ሌላውማ

ትመቸኛለህ ጌታ አሃሃ

ትመችኛለህ ኢየሱስ

ትመቸኛለህ አሃ (፪x)

መልካም ለመሰለኝ በዓይኔ ላየሁት

ፈቃዴን ለማድረግ ልቤን ከሰጠሁት

ጌታዬ ይቅር በለኝ አንተን ለበደልኩት

ቤትህ ይሻለኛል ሰላም የሞላበት

ከአንተው ጋር ልወዳጅ

ከአንተው ጋር ልስማማ (፪x)

ምን ያደርግልኛል ሌላ ሌላውማ

ምን ያደርግልኛል ሌላ ሌላውማ

ትመቸኛለህ ጌታ አሃሃ

ትመችኛለህ ኢየሱስ

ትመቸኛለህ አሃ (፪x)

ወጥቼ ነበረ ድርሻዬን ሰጥተኸኝ

ተመልሼ መጣሁ ጨርሼው አልቆብኝ

ፊትህ አልጠቆረ በርህ አልተዘጋብኝ

አይደለም እንደልጅ ባሪያ አድርገህ ግዛኝ

ከአንተው ጋር ልወዳጅ

ከአንተው ጋር ልስማማ (፪x)

ምን ያደርግልኛል ሌላ ሌላውማ

ምን ያደርግልኛል ሌላ ሌላውማ

ትመቸኛለህ ጌታ አሃሃ

ትመችኛለህ ኢየሱስ

ትመቸኛለህ አሃ (፪x)

ለጊዜው ከሚገኝ ከኃጢአት ደስታ

ሞት ከገነነበት ግርግር ሁካታ

የሰጠኸኝ ሰላም የቤትህ አርካታ

በባዶ ያዘልላል ስሙ የእኔ ጌታ

ከአንተው ጋር ልወዳጅ

ከአንተው ጋር ልስማማ (፪x)

ምን ያደርግልኛል ሌላ ሌላውማ

ምን ያደርግልኛል ሌላ ሌላውማ

ትመቸኛለህ ጌታ አሃሃ

ትመችኛለህ ኢየሱስ

ትመቸኛለህ አሃ (፪x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ