Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ግርም ይለኛል

Gerem Yelegnal

ትራክ 2 · 6:33 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

እግዚአብሔር ግርም ይለኛል (ይለኛል)

እግዚአብሔር ድንቅ ይለኛል (፪x)

መልካም ነው (መልካም ነው)

መልካም ነው (፪x)

መንገድ ላይ ጥሎኝ አልሄደም

ደከመኝ ሰለቸኝ አላለም

እግዚአብሔር ትልቅ ነው እላለሁ (፬x)

ቀንና ሌሊቱ ትልቅ ነህ ይሉታል

መላዕክት ፍጥረቱ ሁሉ ያመልኩታል

አባቶች አምልከው አክብረውት አልፈዋል

በእኔና በቤቴ ጌታ ይመለካል

እግዚአብሔር ግርም ይለኛል (ይለኛል)

እግዚአብሔር ድንቅ ይለኛል (፪x)

መልካም ነው (መልካም ነው)

መልካም ነው (፪x)

የወደቀን ይነሳል ያለው

የሳተውን የሚመልሰው

ኢየሱሴን እወደዋለሁ (፬x)

እንደሌዊ አይደል እንዴት ትቶኝ ያልፋል

ልክ እንደ ካህኑ መች ያፈገፍጋል

ደጉ ጌታ እየሱስ እጁን ይዘረጋል

ቁስሌን በዘይቱ ቀብቶ ያነሳኛል

እግዚአብሔር ግርም ይለኛል (ይለኛል)

እግዚአብሔር ድንቅ ይለኛል (፪x)

መልካም ነው (መልካም ነው)

መልካም ነው (፪x)

ላቆም ነው አልሰግድም ብዬ

አልቀረሁም እሳት ዉስጥ ተጥዬ

ይታመናል ታማኝ ነው ጌታዬ (፬x)

ሰባት እጥፍ ሲነድ ወርውረው ጣሉኝ

የአማልክት አምላክ እዛው አገኘኝ

ኧረ እንዴት ተረፈ ከእሳት ያላችሁ

ከመከራው በፊት እየሱስ ያግኛቹ

እግዚአብሔር ግርም ይለኛል (ይለኛል)

እግዚአብሔር ድንቅ ይለኛል (፪x)

መልካም ነው (መልካም ነው)

መልካም ነው (፪x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ