Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ተመቸኝ

Temechegn

ትራክ 11 · 6:01 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ተመቸኝ/4 እየሱስ

እኔ እንዲ እላለሁ በሰላም ወጥቼ በሰላም ገባለሁ

ስጋት ከኔ እርቆ በእረፍት የኖርኩት

ሚስጥሩ አንድ ነው ጌታን ስለያዝኩት/4

አንገት የሚያስደፉ ነገሮች በሙሉ

በተራ በተራ ከፊቴ ዞር አሉ

እንግዲ ወገኔ ዘመኑ ያንተ ነው

ብለህ ዘምርለት እየሱስ ጌታ ነው/4

እንደ እግዚአብሔር ያለ ቸር አምላክ የት አለ

እንደ እግዚአብሔር ያለ ድንቅ አምላክ የት አለ

ተመቸኝ/4 እየሱስ

እኔ እንዲ እላለሁ በሰላም ወጥቼ በሰላም ገባለሁ

ስጋት ከኔ እርቆ በእረፍት የኖርኩት

ሚስጥሩ አንድ ነው ጌታን ስለያዝኩት/4

በብዙ አልፌ እዚ ደርሻለሁ

ወሃውም እሳቱም ትዛዝ ተቀብለው

ይሽሩን የኔ ነው አሳልፉት ያለው

ማንንም የማይንቅ እግዚአብሔር ትልቅ ነው/4

እንደ እግዚአብሔር ያለ ቸር አምላክ የት አለ

እንደ እግዚአብሔር ያለ ድንቅ አምላክ የት አለ

ተመቸኝ/4 እየሱስ

እኔ እንዲ እላለሁ በሰላም ወጥቼ በሰላም ገባለሁ

ስጋት ከኔ እርቆ በእረፍት የኖርኩት

ሚስጥሩ አንድ ነው ጌታን ስለያዝኩት/4

ሙሴ የፈርዖን የልጅ ልጅ ከመባል

ከእግዚአብሔር ህዝብ ጋር መከራውን መርጧል

ጮማና ወይንጠጅ እንዲንቅ ያረገው

የጌታዬ መና ለኔ እንዴት ድንቅ ነው/4

እንደ እግዚአብሔር ያለ ቸር አምላክ የት አለ

እንደ እግዚአብሔር ያለ ድንቅ አምላክ የት አለ

ተመቸኝ/4 እየሱስ

እኔ እንዲ እላለሁ በሰላም ወጥቼ በሰላም ገባለሁ

ስጋት ከኔ እርቆ በእረፍት የኖርኩት

ሚስጥሩ አንድ ነው ጌታን ስለያዝኩት/4

ሃሌሉያ/8

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ