Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

የራሴ ነገር ስላልጠቀመኝ

Yerasie Neger Selalteqemegn

ትራክ 10 · 5:29 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

የራሴ ነገር ስላልጠቀመኝ

ዋጋ ተምኜ ወጥቻለሁኝ

ጌታን ማገልገል ትርፍ አለውና

ጥማዱን ስበር ስበር ውጣና

የእኔ የራሴ ባልሆነ ነገር

ብዙ ቆየሁኝ ያኔ ስቸገር

ዛሬ ዛሬማ በራልኝና

ድንቁን ራዕይ አየሁኝና

ሁሉንም ነገር ለጌታ ትቼ

እፎይ አረፍኩኝ ተማቻችቼ (፬x)

የራሴ ነገር ስላልጠቀመኝ

ዋጋ ተምኜ ወጥቻለሁኝ

ጌታን ማገልገል ትርፍ አለውና

ጥማዱን ስበር ስበር ውጣና

ታማኝ አድርጐ ስለቆጠረኝ

ለአገልግሎቱ ጌታ የሾመኝ

ሞኞች ቢነቅፉኝ ቢዘብቱብኝ

ትቼ የመጣሁ ባሪያው እኮ ነኝ

እየታገሰ ብርቱ የሚያደርገው

የጌታ መንፈስ በላዬ ላይ ነው (፬x)

የራሴ ነገር ስላልጠቀመኝ

ዋጋ ተምኜ ወጥቻለሁኝ

ጌታን ማገልገል ትርፍ አለውና

ጥማዱን ስበር ስበር ውጣና

ከአባቴ ቤት አስወጣኝ ጌታ

ወዳሳየኝ ሄድኩ ሳላመነታ

እርሱን ታምኜ ስለወጣሁኝ

እረሃቡ ጸና ጥሬ ስላለኝ

ዘርህ እንደአሸዋ ይበዛል እንዳለው

ቃሉን ፈጸመው ተዓምረኛ ነው (፬x)

የራሴ ነገር ስላልጠቀመኝ

ዋጋ ተምኜ ወጥቻለሁኝ

ጌታን ማገልገል ትርፍ አለውና

ጥማዱን ስበር ስበር ውጣና

እናት አባቴ እረስተውኛል

ቸሩ እግዚአብሔር ተቀብሎኛል

የሁሉ ታናሽ የበግ እረኛ

ታላቅ እያለ መርጦ ቀባኛ

እርሱ ሲያጸድቅ ማን ይቃወማል

መቼ በቁመት ልብም ይታያል (፬x)

የራሴ ነገር ስላልጠቀመኝ

ዋጋ ተምኜ ወጥቻለሁኝ

ጌታን ማገልገል ትርፍ አለውና

ጥማዱን ስበር ስበር ውጣና

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ