እፁብ ነህ አንተ
Etsub Neh Ante
ትራክ 8 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
እፁብ ነህ አንተ አንተ አትለወጥም
ግሩም ነህ አንተ ስራህም አያልቅም (፪x)
ቁጥር 1 · Verse 1
እግዚአብሔር አለ በማደሪያው
እግዚአብሔር አለ በዙፋኑ (፪x)
ሰማይ ዙፋንህ ነው ምድር መረገጫ
አለም ዙፋንህ ነው ያንተ መቀመጫ
ሰማይም ያንተ ነው ምድርም ያንተ ነው ሁሉ ግዛትህ ነው
እግዚአብሔር አለ በማደሪያው
እግዚአብሔር አለ በዙፋኑ (፪x)
አዝማች · Chorus
እፁብ ነህ አንተ አንተ አትለወጥም
ግሩም ነህ አንተ ስራህም አያልቅም (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
እግዚአብሔር አለ በማደሪያው
እግዚአብሔር አለ በዙፋኑ (፪x)
ይሁን ይሁን ብለህ የፈጠርከው ሁሉ
ጻድቅነትህን ይመሰክራሉ
እግዚአብሔር አለ እወቁት ይላሉ አክብሩት ይላሉ
እግዚአብሔር አለ በማደሪያው
እግዚአብሔር አለ በዙፋኑ (፪x)
አዝማች · Chorus
እፁብ ነህ አንተ አንተ አትለወጥም
ግሩም ነህ አንተ ስራህም አያልቅም (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
እግዚአብሔር አለ በማደሪያው
እግዚአብሔር አለ በዙፋኑ (፪x)
ከፍ ከፍ ያለውን በሃይሉ አዋርዶ
የሃያላንንም ቀስታቸውን ሰብሮ
በክብር ይኖራል ዘላለም ይገዛል ዙፋኑ ይጸናል
እግዚአብሔር አለ በማደሪያው
እግዚአብሔር አለ በዙፋኑ (፪x)
አዝማች · Chorus
እፁብ ነህ አንተ አንተ አትለወጥም
ግሩም ነህ አንተ ስራህም አያልቅም (፪x)
ቁጥር 4 · Verse 4
እግዚአብሔር አለ በማደሪያው
እግዚአብሔር አለ በዙፋኑ (፪x)
በዘላለም ፍቅሩ ቀድሞ ባቀደው
አለምን ሊያድናት ኢየሱስን ላከው
ሃሳቡ ጸንታለች ማዳኑን አይተናል
ከሀጥያት እስራት ከሞትም ድነናል
እግዚአብሔር አለ በማደሪያው
እግዚአብሔር አለ በዙፋኑ (፪x)
አዝማች · Chorus
እፁብ ነህ አንተ አንተ አትለወጥም
ግሩም ነህ አንተ ስራህም አያልቅም (፪x)
ቁጥር 5 · Verse 5
እግዚአብሔር አለ በማደሪያው
እግዚአብሔር አለ በዙፋኑ (፪x)
ዙሪያው ገደል ሆኖ ግራ ቢገባህም
ጨለማው አይሎ መውጫው ቢጠፋም
እግዚአብሔር አለ እሱ አይተውህም እሱ አይጥልህም
ዙሪያው ገደል ሆኖ ግራ ቢገባሽም
ጨለማ አይሎ መውጫ ቢጠፋሽም
እግዚአብሔር አለ እሱ አይተውሽም እሱ አይጥልሽም
እግዚአብሔር አለ በማደሪያው
እግዚአብሔር አለ በዙፋኑ (፪x)
አዝማች · Chorus
እፁብ ነህ አንተ አንተ አትለወጥም
ግሩም ነህ አንተ ስራህም አያልቅም (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ