ማነው ማነው
Manew Manew
ትራክ 3 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
በኪሩቤል ላይ የተቀመጠው
በሰማይ በምድር ታላቅ የሆነው
ከዙፋኑ ላይ ውረድ የሚለው
እሱን ተክቶ የሚቆም ማነው
አዝማች · Chorus
ማነው ማነው እንዳንተ ማነው (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ከአምላክ በቀር አምላክስ ማነው
ማነው ማነው እንዳንተ ማነው (፪x)
ከአንተ በቀር አምላክስ ማነው
ውሆች በእፍኙ የሰፈረው
ሰማይ በስንዝሩ የለካው
በምን ምሣሌ እንመስለው
ይህን እግዚአብሔር ማን እንበለው
አዝማች · Chorus
ማነው ማነው እንዳንተ ማነው (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
ከአምላክ በቀር አምላክስ ማነው
ማነው ማነው እንዳንተ ማነው (፪x)
ከአንተ በቀር አምላክስ ማነው
ባህርን ከፍሎ የሚያሻግረው
ሰማይን ከፍቶ መና የሚያወርደው
በጸናች ክንዱ የሚታደገው
የእስራኤል አምላክ እርሱ ብቻ ነው
ቁጥር 4 · Verse 4
ማነው ማነው እንደእርሱ ማነው (፪x)
ቁጥር 5 · Verse 5
ከእርሱስ በቀር አምላክስ ማነው
ማነው ማነው እንዳንተ ማነው (፪x)
ከአንተ በቀር አምላክስ ማነው
ክንዱ አይዝልም የምናመልከው
ሁሌ ብርቱ ነው የማይታክተው
ይሄ አምላካችን ዛሬም ሕያው ነው
ተወዳዳሪ መሳይ የሌለው
አዝማች · Chorus
ማነው ማነው እንዳንተ ማነው(፪x)
ቁጥር 6 · Verse 6
ከአንተ በቀር አምላክስ ማነው
ማነው ማነው እንደእርሱ ማነው (፪x)
ከእርሱስ በቀር አምላክስ ማነው
በነፃ ብሉ ጠጡ የሚለው
ዋጋ ማይጠይቅ ማያስከፍለው
አንድያ ልጁን ወዶ ሚሰጠው
ከእግዚአብሔር በቀር ወዳጅስ ማነው
አዝማች · Chorus
ማነው ማነው እንዳንተ ማነው (፪x)
ቁጥር 7 · Verse 7
ከአንተ በቀር አምላክስ ማነው
ማነው ማነው እንዳንተ ማነው (፪x)
ከአንተ በቀር ወዳጅስ ማነው
ሁሉን ይቀርባል እሩህሩህ ነው
እንደሰው አይደል አይሰለቸው
ወረትን አያውቅ ጊዜ አይለውጠው
እግዚአብሔር አምላክ እግዚአብሔር ነው
አዝማች · Chorus
ማነው ማነው እንዳንተ ማነው (፪x)
ቁጥር 8 · Verse 8
ከአምላክ በቀር አምላክስ ማነው
ማነው ማነው እንዳንተ ማነው (፪x)
ከአንተ በቀር አምላክስ ማነው (፫x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ