ለሰው አላወራም
Lesew Alaweram
ትራክ 9 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ለሰው አላወራም ምን ትርፍ አገኛለሁ
ሃዘኔን ብሶቴን ላንተው እነግራለሁ
ደጃፌን ዘግቼ አጫውትሃለሁ
አምናለሁ ካንተ ዘንድ ምላሽ አገኛለሁ (፪x)
አዝማች · Chorus
የሚያስጨንቀኝን ላንተው እነግራለሁ
ትካዜዬን ሁሉ በአንተ ላይ እጥላለሁ
የመድኃኒቴ አምላክ ተስፋ አረግሃለሁ (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
የኤርትራን ባህር ታሻግረኛለህ
ከሰማያት መናን ታወርድልኛለህ
ሃሳብህም ከቶ አይከለከልም
ሁሉ ይቻልሃል ምንም አይከብድህም (፪x)
አዝማች · Chorus
የሚያስጨንቀኝን ላንተው እነግራለሁ
ትካዜዬን ሁሉ በአንተ ላይ እጥላለሁ
የመድኃኒቴ አምላክ ተስፋ አረግሃለሁ (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
የነገሩህንም የማትረሳ ነህ
አንዱም አይጠፋህም ታስታውሰዋለህ
ሕመሜን በሙሉ አንተ ታውቀዋለህ
መድኃኒቴ አንተ ነህ ትፈውሰኛለህ (፪x)
አዝማች · Chorus
የሚያስጨንቀኝን ላንተው እነግራለሁ
ትካዜዬን ሁሉ በአንተ ላይ እጥላለሁ
የመድኃኒቴ አምላክ ተስፋ አረግሃለሁ (፪x)
ቁጥር 4 · Verse 4
::የመድኃኒቴ አምላክ ተስፋ አረግሃለሁ (፫x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ