ጐልጐታ ትመስክር
Golgota Timeskir
ትራክ 4 · 6:23 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ጐልጐታ ትመስክር ቀራንዮ ትናገር
የጌታ ኃይል ጣሩን የአኳሃኑን ነገር
አዝማች · Chorus
ከዚህስ የሚበልጥ ፍቅር የለም
ቁጥር 2 · Verse 2
ከኢየሱስ የሚበልጥ ፍቅር የለም
ከአምላኬ የሚበልጥ ፍቅር የለም
ከጌታ የሚበልጥ ፍቅር የለም
ነፍሱን ስለእኔ የሚያሰጥ መውደድ
መስቀል አሸክሞ አስጐንብሶ የሚያስኬድ
የጌታዬን ፍቅር ምን ይመጥነዋል
ከምንም ከምንም ከምንም ይበልጣል
ቁጥር 3 · Verse 3
ከኢየሱስ የሚበልጥ ፍቅር የለም
ቁጥር 4 · Verse 4
ከዚህስ የሚበልጥ ፍቅር የለም
ከአምላኬ የሚበልጥ ፍቅር የለም
ከጌታ የሚበልጥ ፍቅር የለም
እንዴት እንዲወደኝ እኔ የማውቀው
የተወጋ ጐኑን እሱን ሳየው ነው
የእሾህ አክሊል አርጐ አንገቱን የደፋው
እኔን ደስ ብሎኝ ስቄ እንድኖር ነው
አዝማች · Chorus
ከዚህስ የሚበልጥ ፍቅር የለም
ቁጥር 5 · Verse 5
ከኢየሱስ የሚበልጥ ፍቅር የለም
ከጌታ የሚበልጥ ፍቅር የለም
ከአምላኬ የሚበልጥ ፍቅር የለም
ደም ግባት ውበትን የሌለው ተባለ
ስለበደሌ ሲል ደቀቀ ቆሰለ
አፉን አልከፈተም አምላኬ ዝም አለ
ሕመሜን ታመመ ደዌን ተቀበለ
አዝማች · Chorus
ከዚህስ የሚበልጥ ፍቅር የለም
ቁጥር 6 · Verse 6
ከኢየሱስ የሚበልጥ ፍቅር የለም
ከአምላኬ የሚበልጥ ፍቅር የለም
ከጌታ የሚበልጥ ፍቅር የለም
ሀዘኔን ምሬቴን በሰፍነጉ ሞልቶ
ኢየሱሴ ጠጣልኝ ከሰማያት መጥቶ
ሁሉን ጨርሶታል ምንም አላስቀረም
ለኔ ያስተረፈው ኾምጣጤኮ የለም
አዝማች · Chorus
ከዚህስ የሚበልጥ ፍቅር የለም
ቁጥር 7 · Verse 7
ከዚህስ የሚበልጥ ፍቅር የለም
ከአምላኬ የሚበልጥ ፍቅር የለም
ከጌታ የሚበልጥ ፍቅር የለም
ጐልጐታ ትመስክር ቀራንዮ ትናገር
የጌታ ኃይል ጣሩን የአኳሃኑን ነገር
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ