ያላንተ ኑሮ
Yalante Nuro
ትራክ 2 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ያላንተ ኑሮ አይሆንልኝም ጌታዬ አይሆንልኝም
ቁጥር 2 · Verse 2
እኔስ ያላንተ አይሆንልኝም ጌታዬ አይሆንልኝም
ወጣሁ ወረድኩ ብዙ አየሁኝ
እንዳንተ የሚሆን መቼ አገኘሁኝ
ድካሜ ሁሉ ከንቱ ነበረ
አንተ ስትመጣ ሕይወቴ አማረ
አዝማች · Chorus
ታዲያ ያላንተ እንዴት አድርጌ እኖራለሁ እንዴት አድርጌ
ያላንተ ኑሮ አይሆንልኝም ጌታዬ አይሆንልኝም
ቁጥር 3 · Verse 3
የዓለም ፍቅር ተሟጦ ያልቃል
ያንተ ፍቅር ግን መቼ ያረጃል
አትጠገብም ቀርቦ ላየህ
አቤት ጌታዬ ምን አይነት ነህ
አዝማች · Chorus
ታዲያ ያላንተ እንዴት አድርጌ እኖራለሁ እንዴት አድርጌ
ያላንተ ኑሮ አይሆንልኝም ጌታዬ አይሆንልኝም
ቁጥር 4 · Verse 4
የአሕዛብ ኑሮ ሁሌ ይደንቀኛል
ሰው ካለ ኢየሱስ እንዴት ይኖራል
አንተን ያጣ ሰው ያልታደለ ነው
ከርታታ መና ተስፋ የሌለው
ቁጥር 5 · Verse 5
እኔስ ኑሮ አይሆንልኝም ጌታዬ አይሆንልኝም
ቁጥር 6 · Verse 6
እኔስ ያላንተ አይሆንልኝም ኢየሱስ አይሆንልኝም
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ