ማራናታ
Maranatha
ትራክ 10 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
ማራናታ (፫x)
ቶሎ ና ፤ የኔ ጌታ ፤ የኔ ጌታ (፪x)
ቁጥር 1 · Verse 1
ቃልህን በመግለጥ፧ ዓለምን ሙላና
በድንቅ በተዓምር ተመላለስና
አንተን ተቀብለው ነፍሳት ይዳኑና
የኔ ጌታ ኢየሱስ እባክህ ቶሎ ና
አዝማች · Chorus
ማራናታ (፫x)
ቶሎ ና ፤ የኔ ጌታ ፤ የኔ ጌታ
ቁጥር 2 · Verse 2
እመጣለሁ ብለህ ቃል ገብተህልናል
ቃልህ እንዲፈጸም ልጆችህ ናፍቀናል
የታረደውን በግ ስለበደላችን
ልናይ እንወዳለን ሁላችን በዓይናችን
አዝማች · Chorus
ማራናታ (፫x)
ቶሎ ና ፤ የኔ ጌታ ፤ የኔ ጌታ
ቁጥር 3 · Verse 3
በዕንቁ በወርቅ አርጐ እግዚአብሔር የሰራት
ጥላቻ ተረስቶ ፍቅር የሞላባት
ለእኛ ለልጆቹ አምላክ ያዘጋጃት
ኢየሩሳሌምን መቼ ነው የማያት
አዝማች · Chorus
ማራናታ (፫x)
ቶሎ ና ፤ የኔ ጌታ ፤ የኔ ጌታ (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ