ጌታ ይሻልሃል
Gieta Yeshalehal
ትራክ 5 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ጣል ጣል አታርጊው ኢየሱስን ውደጂው (፪x)
ደግሞም አትናቂው ክብርን ለሱ ስጪው (፪x)
ዓይንሽ ያረፈበት እሱ ያጠፋሻል (፪x)
ተይ ተይ አትወላውይ ጌታ ይሻልሻል (፪x)
አዝማች · Chorus
ጌታ ይሻልሻል ጌታ ይሻልሻል ኢየሱስ ይሻልሻል
ኢየሱስ ይሻልሃል ኢየሱስ ይሻልሃል ጌታ ይሻልሃል
ቁጥር 2 · Verse 2
ነገ ዛሬ አትበል ኢየሱስን ተቀበል (፪x)
የሚያባብልህን ዓለምን እምቢ በል (፪x)
ከታሰርክበትም እርሱ ይፈታሃል (፪x)
ቀረብ በል ተጠጋ ጌታ ይሻልሃል (፪x)
አዝማች · Chorus
ጌታ ይሻልሻል ጌታ ይሻልሻል ኢየሱስ ይሻልሻል
ኢየሱስ ይሻልሃል ኢየሱስ ይሻልሃል ጌታ ይሻልሃል
ቁጥር 3 · Verse 3
የሚያታልለውን የሱን ቃል አትስሚ (፪x)
ይልቅስ ከአምላክሽ ከእግዚአብሔር ተስማሚ (፪x)
ሊሰርቅና ሊያድ ሊያጠፋሽ ነውና (፪x)
ነይ ነይ ወደ ኢየሱስ እሱን ተይውና (፪x)
አዝማች · Chorus
ጌታ ይሻልሻል ጌታ ይሻልሻል ኢየሱስ ይሻልሻል
ኢየሱስ ይሻልሃል ኢየሱስ ይሻልሃል ጌታ ይሻልሃል
ቁጥር 4 · Verse 4
እስኪ ወንድሜ ሆይ ተስፋህ ምንድነው (፪x)
ምንም ነገር የለ እስኪ አስበው (፪x)
በዚህ ክፉ ዘመን ሰብሰብ በልና (፪x)
አረፍ በል ተቀመጥ ኢየሱስን ያዝና (፪x)
ቁጥር 5 · Verse 5
ጌታ ይሻልሃል ጌታ ይሻልሃል ኢየሱስ ይሻልሃል
ቁጥር 6 · Verse 6
ኢየሱስ ይሻልሻል ኢየሱስ ይሻልሻል ጌታ ይሻልሻል
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ