እወድሃለሁ
Ewedehalehu
2010 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
በባዶነቴ አግኝተኀኛል
አንተ እኔን መውደድ ያስገርመኛል
አወዳደድህ ከመውደድ ያልፋል
ወደድኩህ ብልህ ምን ያስገርማል
ለምንድን ነው አልልህም
ስራህ ጠፍቶኝ አልጠይቅህም
የምልህ ግን አንድና ግልጽ ነው
ስለወደድከኝ ወድጄሃለሁ
አዝማች · Chorus
እወድሃለሁ አሳብዬ
እወድሃለሁ (፪x)
ስለወደድከኝ አሳብዬ
ወድጄሃለሁ (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ወድጄሃለሁ ወድጄሃለሁ
ለመውደዴ ገደብ የለኝም
ምገልጸበት ቋንቋም አላገኝም
ብቻ ነፍሴ አፍቅራሃለች
እንደወደድካት ትወድሃለች
አዝማች · Chorus
እወድሃለሁ አሳብዬ
እወድሃለሁ (፪x)
ስለወደድከኝ አሳብዬ
ወድጄሃለሁ (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
የአንተ ፍቅር መውደድህ አያልቅም
መውደዴ ግን የአንተን ፍፁም አይገልጸውም
አይገልጸውም ብዬ እንዴት ዝም እላለሁ
በትንሿ ልቤ አቅሜ ቢሆንም ይሄው እወድሃለሁ
አዝማች · Chorus
እወድሃለሁ አሳብዬ
እወድሃለሁ (፪x)
ስለወደድከኝ አሳብዬ
ወድጄሃለሁ (፪x)
ቁጥር 4 · Verse 4
እወድሃለሁ (፫x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ