ይቅር በለን
Yeqer Belen
2010 · 6:15 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ሰው መሆኑን አይደል ልብሱን አከበረ
ሰው በገንዘቡ ልክ ወዳጅ አስቆጠረ (አቤት አቤት)
ምስኪኑ ሲመጣ አጥቶ የሚቀምሰው
የሚቀርበው ጠፍቶ ፍቅር እንኳን ከራቀው
አቤት አቤት አቤቱ ምን አልከው
አዝማች · Chorus
አቤቱ አትታዘበን
እንመለሳለን ይቅር በለን (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ምሕረቱን ተማምነን አይተን እንደዋዛ
የድፍረታችን ልክ ሃጥያታችን በዛ
ታጋሽ ሳይፈርድብን ቁጣውን ሳይልከው
ይብቃን እንመለስ ዝምታው ምክር ነው
የቤትህ አገልጋይ ስንቱን ሕዝብ አሰረው
የሚያወራው አፉ ልቡ ግን ሌላ ነው (አቤት አቤት)
ተግባር የለሽ ምክሩ ለራሱም ካልበጀው
ልጅ አባቱ ታሞ እንዴት ይመልሰው
አቤት አቤት አቤቱ ምን አልከው
አዝማች · Chorus
አቤቱ አትታዘበን
እንመለሳለን ይቅር በለን (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
ያከበርከው ትዳር ያቀናኸው ጎጆ
ሊዘልበት ጠላት ተንዶ ተንዶ (አቤት አቤት)
እንደ አሸዋ ሲርድ ከአለት ያፀናኸው
እሌላ ሲከጅል በክብር የዳርከው
አቤት አቤት አቤቱ ምን አልከው
ምሕረቱን ተማምነን አይተን እንደዋዛ
የድፍረታችን ልክ ሃጥያታችን በዛ
ታጋሽ ሳይፈርድብን ቁጣውን ሳይልከው
ይብቃን እንመለስ ዝምታው ምክር ነው
መስሎት የተማረ በልጦበት እውቀቱ
አምላክ የለም አለኝ ኢኸው እንደልቡ ይህ ሰው (አቤት አቤት)
የአመፃው ብዛት ሃጥያቱም ሲከፋ
ሴት ለሴት ተዳረች ወንድም ወንድ አገባ
አቤት አቤት አቤቱ ምን አልከው
አዝማች · Chorus
አቤቱ አትታዘበን
እንመለሳለን ይቅር በለን (፪x)
ቁጥር 4 · Verse 4
ለተመቸው እርሙ መች ይቅርታን ያውቃል
ይልቅ ለጥፋቱ ጥቅስ ይሸራርፋል ይህ ሰው አቤት አቤት
መውጣቱስ ይክበደው አጠፋሁ ቢል ምነው
እራስን አታሎ መጨረሻው የት ነው
አቤት አቤት አቤቱ ምን አልከው
ምሕረቱን ተማምነን አይተን እንደዋዛ
የድፍረታችን ልክ ሃጥያታችን በዛ
ታጋሽ ሳይፈርድብን ቁጣውን ሳይልከው
ይብቃን እንመለስ ዝምታው ምክር ነው
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ