Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ወንጌል ሰላም

Wengiel Selam

2010 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ይነገር ለዓለም ቅዱሱ መጽሃፍ

ከዳር ዳር ይሰማ እውነቱ አይታለፍ

ዘር ቀለም ላይለየው ለሁሉም ተፈቅዷል

ለወደዱት ሁሉ ሰላምን ይሰጣል

ወንጌል መሪ ወንጌል ሰላም

ለሰው ልጆች ይሁን መዳን

ለህዝባችን ይሁን መዳን (፪x)

የታሰሩ ይፈታሉ የታመሙት ይድናሉ

ይፈታሉ ይድናሉ ፈውስ ነው ወንጌሉ

(ኡዎዉዎዎ) ፈውስ ነው ወንጌሉ ፈውስ ነው ወንጌሉ (፪x)

ሊታረም የማይችል ፍፁም እውነት አለው

ሊሽረው የቆመ የትኛው ጠቢብ ነው

የጠቢባን ጠቢብ ይህን ከገለጸው

የደህንነት መንገድ ኢየሱስ ብቻ ነው

ወንጌል መሪ ወንጌል ሰላም

ለሰው ልጆች ይሁን መዳን

ለህዝባችን ይሁን መዳን (፪x)

የታሰሩ ይፈታሉ የታመሙት ይድናሉ

ይፈታሉ ይድናሉ ፈውስ ነው ወንጌሉ

(ኡዎዉዎዎ) ፈውስ ነው ወንጌሉ ፈውስ ነው ወንጌሉ (፪x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ